ፅዱ እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ የጎላ ሚና ያለው ብሔራዊ ሰሠርኩላር ኢኮኖሚ ፍኖተ ካርታን ይፋ ሆነ።
ሐምሌ 21 2017 ዓ ም
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር በመተባበር ለሀገር በቀል ኢኮኖሚ ትግበራ እና ለዘላቂ የአካባቢ ሐብት አጠቃቀም ጉልሕ አስተዋፅኦ እንዳለው የታመነበት ብሔራዊ ሰሠርኩላር ኢኮኖሚ ፍኖተ ካርታን ይፋ አደረገ።
የኢፌዲሪ መንግሥት ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ዕቅድን በመተግር ፅዱ እና የበለፀገች ኢትዮጽያን ለትውልድ ለማውረሥ በርብርብ ላይ መሆኑ የሚታወቅ ነው ። የዚሁ ብሔራዊ ዕቅድ አንደኛው የማስፈፀሚያ ሥልት አካል የሆነው ብሔራዊ ሰሠርኩላር ኢኮኖሚ ፍኖተ ካርታ ዛሬ ጠቀሜታውን እንዲሁም አተገባበሩን ባመላከተ መልኩ ከተለያየ ዘርፍ ለተወከሉ ኃላፊዎች፣ ባለሙያዎች እና የመገናኛ ብዙሀን ቀርቧል።
በሒልተን ሁቴል በተዘጋጀው የትውውቅ እና የትግበራ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር ላይ የተገኙት የአፍሪካ ልማት ባንክ ቢሮ ተወካይ አቶ መንግሥቱ በቀለ ፍኖተ ካርታውን አስመልክተው ባቀረቡት ንግግር የኢትዮጽያ ሕዝብ ውጋጅን መልሶ መጠቀም ልምድ እንዳለው በማስታወስ ወደ ትግበራ በሚገባበት ወቅት ፈርጀ ብዙ ማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንደሚያስገኝ አስረድተዋል።
የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሪክተር ኢ/ር ለልሴ ነሜ በበኩላቸው የብሔራዊ ሰሠርኩላር ኢኮኖሚ ፍኖተ ካርታ ለፅዱ እና የበለፀገች ኢትዮጽያ ምን ምን አብይ ጠቀሜታ እንዳለው ገለፃ አድርገዋል።
ክብርት ኢንጅነር በገለፃቸው ብሔራዊ ሰሠርኩላር ኢኮኖሚ ፍኖተ ካርታን ሲተገበር :-
# ብክለት እና ብክነትን በመቀነሥ ዘላቂ የአካባቢ ሐብት አጠቃቀም መርህን በተሟላ መልኩ መተግበር ማስቻሉን።
# የካርበን ልቀትን በመቀነሥ አካባቢ ላይ የሚደርሥን ጫና ማስቀረቱ።
# ሀገራዊ የውጋጅ ሐብትን መልሶ መጠቀምን በማበረታታት ከኢኮኖሚያዊ ጥገኝነት ማላቀቁን።
# ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት የራሱ አበርክቶ መሥጠቱን እንዲሁም
# የፈጠራ ክህሎትን በማዳበር እና በፋክክር መሀል የሚፈጠርን ጤናማ ውድድር በማላቅ ለአረንጓዴ የሥራ ዕድል ፈጠራ ግሩም አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት አሰረድተዋል።
በብሔራዊ ሰሠርኩላር ኢኮኖሚ ፍኖተ ካርታ ትውውቅ እና ማስጀመሪያ መድረክ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ለትግበራው የየበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንደሚያበረክቱ ተናግረዋል።
ፅዱ እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ ጠቀሜታ እንዳለው የታመነበት ብሔራዊ ሰሠርኩላር ኢኮኖሚ ፎኖተ ካርታ በቀጣይ ከተለያዩ አካላት ጋር በሚደረግ የጥምረት ስራ ተግባራዊ እደሚሆን በመድረኩ ተገልፃል።