ፅዱ ኢትዮጽያን ባህል እናድርግ በሚል መሪ መልዕክት እየተካሔደ የሚገኘው የተማሪዎች የጥያቄ እና መልሥ ውድድር ተጠናክሮ ቀጥሏል
ለሚኩራ ክፍለከተማ
አዲሥ አበባ
========================================================================
የአካባቢ ልማት፤ እንክብካቤንና ጥበቃን በዜጎች አእምሮ በማስረፅ ዘላቂነት ያለው የአካባቢ ሀብት አጠቃቀምን ለማስፈን በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛል ።
የዚሁ ተግባር አንድ አካል የሆነው እና ፅዱ ኢትዮጽያን ባህል እናድርግ በሚል መሪ መልዕክት እየተካሔደ የሚገኘው የተማሪዎች ጥያቄ እና መልሥ ውድድር ዛሬ በጎሮ ቅድመ አንደኛ ፣መካከለኛ እና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ተካሒዷል።
የተካሔደው የጥያቄ እና መልሥ ውድድር በይዘቱ የአካባቢ ልማት፤ እንክብካቤና ጥበቃ ምንነትን ፣ ስስ ፌስታል በአካባቢ እና ማኅበረሰብ ስለሚያስከትለው ጠንቅ፣ እንዲሁም የፅዱ ኢትዮጵያን መሰረታዊ ሃሳቦች ያንፀባረቀ ነው።
በዕለቱ በተካሔደው የጥያቄ እና መልሥ ውድድር ብልጫ ላሳዮ ተማሪዎች እንደወትሮው የማበረታቻ ሽልማት ተሰጥቷል።
ፅዱ ኢትዮጽያን ባህል እናድርግ በሚል መሪ መልዕክት እየተካሔደ የሚገኘው የተማሪዎች የጥያቄ እና መልስ ውድድር በሌሎች ክፍለከተሞች እንደሚቀጥል ታውቋል።
========================================================================