ፅዱ ኢትዮጵያን ባህል ለማድረግ ሚዲያዎች ያላቸውን ሚና በተመለከተ ፓናል ውይይት ተካሄደ።
ግንቦት 2017ዓ.ም
ግንቦት 28/2017 ዓ.ም
"""""'''''''''''''''''''''''"""""""""'''''''''''''''''''''''""""@"""""'''''''''''''''''''''''"""""""""'''''''''''''''''''''''""""
የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ያስጀመረውን ፅዱ ኢትዮጵያን ባህል ማድረግ ንቅናቄ ውጤታማነት ለማረጋገጥ ሚዲያዎች ያላቸውን ሚናን በተመለከተ ከሚዲያ ተቋማት ጋር ውይይት ተካሂዷል።
የፓናል ውይይቱ የክብር እንግዳ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሙዓዛ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት እንደገለፁት ኢትዮጵያን ፅዱና አረንጓዴ ማድረግ ባህል እየሆነ መምጣቱን በመግለፅ ተከታታይነት ያለው ስራ መሰራት እንደሚጠበቅ ጠቁመው የሚዲያ ተቋማት ፅዱና አረንጓዴነትን ባህል ለማድረግ ግንዛቤውን ለሁሉም ማህበረሰብ ተደራሽ ማድረግ፣ የሚዲያ ተቋማት ራሳቸው የፅዳትና አረንጓዴነት ምሳሌ መሆን እንዲሁም ፅዳትና አረንጓዴነት ባህል ሆኖ እንዲቀጥል መስራት እንደሚገባቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ም/ዳይሬክተር ክቡር አቶ ንጉሱ ለማ በበኩላቸው ባለስልጣኑ ያስጀመረው ንቅናቄ ለቀጣይ ስድስት ወራት እንደሚካሄድ በመግለፅ ለስኬቱ የሚዲያ አካላት ሚና ጉልህ መሆኑን በመጥቀስ ለውጤታማነቱ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲወጡ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
ንቅናቄው በፕላስቲክ ብክለት፣በአፈርና ውሃ ብክለት፣በአየር ብክለት፣በቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ፣በድምፅ ብክለትና በአካባቢና ማህበራዊ ተፅዕኖ ግምገማ ውጤታማነት ላይ በማተኮር የሚካሄድ ነው።
====================================
የኢፌዲሪ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን
ቀጣዮችን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ