የ''ፅዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ'' ክልል አቀፍ የአካባቢ ብክለት መከላከል ንቅናቄ በሀረሪ ክልል በሃራር ከተማ በይፋ ተጀመረ ::
ሐምሌ 5/12/2018 ዓ.ም
ሀረር
====================
''ፅዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ''ሶስተኛው ዙር ክልል አቀፍ የአካባቢ ብክለት መከላከል ንቅናቄ በሀረሪ ክልል የክልሉ የሀረሪ ጉባኤ ም/ቤት ዋና አፈጉባኤ ክቡር ሙሀዲን አህመድ፣ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ ጌቱ ወዬሳ፣ ክብርት ወ/ሮ ፍሬነሽ መኩሪያ የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር ፣የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ፣ የተለያዩ የግሉ ዘርፍ ማህበራት፣ የፀጥታ አባላት፣ የወረዳ አመራሮች የት/ቤቶች ተማሪዎችና መምህራን፣ የአካባቢ ተዋቂ የሀገር ሽማግሌዎችና የባህል አባቶች፣ የሃይማኖት አባቶች እና የሀረር ከተማ ነዋሪዎች በተገኙበት በተለያዩ ኩነቶች በይፋ ተጀመሯል።
የክልሉ የሀረሪ ጉባኤ ም/ቤት ዋና አፈጉባኤ ክቡር አቶ ሙሀዲን አህመድ የክልል አቀፍ የንቅናቄ መድረኩን በንግግር በይፋ ባስጀመሩበት ወቅት በሀገራችን እየተሰሩ የሚገኙ የልማት ሥራዎች ሀገራችንን ከድህነትና ኋለቀርነት በማስለቀቅ የህዝቦቡን ኑሮ ከማሻሻል አንፃር ወሳኝ መሆኑን በመንሳት ነገር ግን ልማት አካባቢንና የሰዎችን ጤና የሚያውክ እንዳይሆን ለአካባቢ ጥበቃ ትከረት በማድረግ መከናወን እንዳለባቸው አሳስበዋሉ፡፡
በአሁኑ ወቅት በሀገራችን እየተሰሩ የሚገኙ የከተሞች ኮርደር ልማት ከተሞችን ፅዱ ከማድረጉም በላይ ለነዋሪዎቹ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ከማስገኘት አንፇር ፋይዳው የላቀ መሆኑ አንስተው፤ በግልም ይሁን በመንግታዊ ተቋማት የሚሰሩ የልማት ሥራዎች የአካባቢ ደህነቱንና የተፈጥሮ ሀብት ሥርዓተ ምህዳሩን በጠበቀ መንገድ እንዲከናውኑ ጥሪ አስተላልፈዋሉ፡፡
የሚሰሩ የልማት ሥራዎች በሰዎች ጤና፣ በአካባቢ ደህንነት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንይፈጥሩ እንዲሁም የአካባቢ ሥርዓተ ምህዳሩን እንዳያዘቡ በመንግስት የወጡ ህጉችንና አሰራሮችን መሠረት በማድረግ እንዲፈፀም፤ ህጎቹን በማያከብሩት ላይ ደግሞ የህግ ተከባሪነትን ማረጋጋጥ እንደሚገባ፣ እንደ ሀገር የተጀመረው የፅዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ ንቅናቄ በክልላችን ውጤታማ እንዲሆን በአግባቡ እየተመራ በቅንጅት መሠራት እንዳለበት በአጽዕኖት አሳስበዋሉ።
የፌደራል አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፍሬነሽ መኩሪያ ባስተላለፉት መልዕክት በአሁኑ ወቅት ከህዝብ ቁጥረር ዕድገት፣ ከንግድ ና ገንባታ መጨመር፣ ከከተሞች መስፋፋት ጋር ተያያዞ አለማችን ብዚ የአካካቢ ችግሮችን በተለይ የአካባቢ ብክልት፣ የብዝሃ ህይወት መጥፋትና የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕና እጅግ እያሰሳ መሆኑ በመንሳት ሀገራት ችግሮችን ለመፍጠተት ዘርፈ ብዙ ተግባራትን በማከናወን ካይ ይገኛል ብለዋሉ፡፡
አካባቢን ከብክለት መከላከል የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ቀጣይነት ማረጋገጥ በመሆኑ በአካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ሁሉም ዜጋ የአካባቡ ብክልት የሚያስከትለውን የ ሰዎች ጤና መታወክ፣ምርትና ምርታመነት መቀነስ፣ የተፈጥሮ ሀብቶችቻችን መውደምና መራቆት የብዝሃ ህይወት መመናመን አሳሳቢነቱን ለመለው ህዝባችን ለማስገነዝብ ተሳትፎአቸውንም ለማሰደግ ከዚህ በፍት እንደ ሀገር በተካሄዱ ሁለት ዙር ንቅናቄዎች በአካባቢ ጥበቃ፣ በተፈጥሮ ሀብቶች አጠባበቅ መሻሻል የተገኙ ውጤቶችን በጋራ በመገምገም ውስንነቶችን ደግም በመለየት በቀጣይ ለማስተካከል እንዲቻል፤ እስካሁን በንቅናቄዎቹ በተፈጠረው ግንዛቤ በየአካባቢው የተፈጠረውን ከፍተኛ መነቃቃትን በመጠቀም በቀጣይ ለበለጠ ውጤት በትጋትና በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ገልፀዋሉ፡፡
ዛሬ በሚካሄደው ክልል አቀፍ የአካባቢ ብክለት መከላካል ንቅናቄ መድረክም በቀጣይ ሶስት ወራት በፕላስቲክ ፣ በአደገኛ ኬምካሎችና ቆሻሻ እና በድምጽ ብክለትን ለመከለከል በቅንጅት ነሚሰራ በመሆኑ ሁሉም የሚመለከታቸውን አካላትን በማቀናጀት መፈፀም እንደሚጠበቅ አሳስበዋሉ።
የፌደራል አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ክቡርት ወ/ሮ ፍሬነሽ መኩሪያ ባስተላለፉት መልዕክት አካባቢን ከብክለት መከላከል ማህበራዊና ኢኮኖሚ ልማትን ቀጣይነት ማረጋገጥ በመሆኑ ከዚህ በፍት እንደ ሀገር በተካሄዱ ሁለት ዙር ንቅናቄዎች በአካባቢ ጥበቃ፣ በተፈጥሮ ሀብቶች አጠባበቅ መሻሻል የተገኙ ውጤቶችን በጋራ በመገምገም ውስንነቶችን ደግም በመለየት በቀጣይ ለማስተካከል እንዲቻል ፤ እስካሁን በንቅናቄዎቹ በተፈጠረው ግንዛቤ በየአካባቢው የተፈጠረውን ከፍተኛ መነቃቃትን በመጠቀም በቀጣይ ለበለጠ ውጤት በትጋትና በቅኝጅት መስራት እንደሚገባውም አሳስበዋሉ።
የሀረሪ ክልል አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ናቢላ ሙህዲን በበኩላቸው አካባቢ መጠበቅ ህናማ አካባቢን ለማስፈን እንደክልል ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን በማከናወን ላይ መሆን በንሳት በቅድሚያ ለማህበረሰቡ በአካባቢ ችግሮች፣ የሚከሰትበት ምክንያቶች፣ ብክለትን በሚንከላከልበት ሁኔታዎች እና በአካባቢ ህጎች ላይ ግንዛቤ መፍጠር የአመለካከትና የአስተሳሰብ ለውጥ ማምጣት ወሳኝ በመሆኑ ይህ ዛሬ በክልላችን የሚጀመረውን የግንዛቤ ማስጨበጫ ንቅ መድረኩን አንዱ ነው ብለዋሉ፡፡
አካባቢን ከብክለት በመከላከል ለህዝቦቻችን ምቹ አካባቢን መፍጠር የሁሉም ባለድርሻ አካላትና የዜጎችም ሁሉ ኃላፊነት በመሆኑ በዚህ ፅዱ ኢትዮጸጵያ ለትውልድ ንቅናቄ በመሳተፍ የበኩላቸው እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋሉ።
በመጨረሻም መድረኩም የፌደራልና ክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እና የተለያዩ ከተማው የህብረሰብ ክፍሎች እና የሀረር ከተማ ነዋሪዎች በተገኙበት በአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተካለ ተጀምሮ ለፓናል ውይይት መነሻ ሰነድ ቀርቦ በክልሉ ጤና ቢሮ፣ የከተማ ማዘጋጀ ቤት ሥራ አስኪያጅ እና የክልሊ የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊዎች የፓናል ውይይት ተደርጎ የዕለቱ መድረኩ ተጠናቋል፡፡