የፕላስቲክ ከረጢቶች በሰው ጤና እና በአካባቢ ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት በሚመለከት ተከታታይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ለተማሪዎች በመሰጠት ላይ ይገኛል ፡፡
ታህሳስ 7/2018 ዓም
አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
አንድ ጊዜ አገልግሎት የሚሰጡ ስስ የፕላስቲክ ከረጢቶች መጠቀም በህጉ መሰረት ከጥር 23/2018 ዓ.ም ጀምሮ ክልከላ ይጀምራል፡፡ይህንኑ ምክንያት በማድረግ ለተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች የግንዛቤ ማስጨበጫ መሰጠቱ ይታወሳል፡፡ የዚሁ አካል የሆናው የፕላስቲክ ከረጢቶች በሰው ጤና እና በአካባቢ ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት በሚመለከት ተከታታይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ለተማሪዎችም እየተሰጣ ይገኛል ፡፡
በዛሬ እለትም የጽዱ ኢትዮጵያ ባህል ማድረግ የቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ ግንዛቤ ለማስጨበጥ በአዲስ አበባ አስተዳደር አረዳ ክ/ከተማ ዳግማዊ ሚኒሊክ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ግንዛቤ የተማሪዎች ጥያቄ እና መልስ ውድድር ተካሄዷል፡፡
ተማሪዎች የፕላስቲክ ከረጢቶች ጉዳት በመረዳት ከቤተሰብ ጀምሮ መላው ህብረተሰቡን ግንዛቤ እንዲያስጨብጡ መልዕክት ተላልፏል፡፡ በመጨረሻም ተማሪዎች ይህንን አውቀው ቤተሰቦቻቸው አካባቢን የማይበክሉ መያዣዎችን እንዲጠቀሙ መልዕክት እንድያስተላልፉላቸው ተጠይቀዋል፡፡
====================================