የገንዘብ ሚኒስቴር እና ፕላንና ልማት ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማት ጋር 7ኛዉ ሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራ "በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ሀሳብ የችግኝ ተከላ አካሄደ፡፡
ሐምሌ 1/2017 ዓ.ም
@**
የገንዘብ ሚኒስቴር እና ፕላንና ልማት ሚንስቴር እንድሁም ተጠሪ ተቋማት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ጋር በመተባበር በመትከል መንሰራራት በሚል የ7ኛ ሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራ የተለያዩ ሀገር በቀል ችግኝ ተከለ እና ጽዱ ኢትዮጵያን ባህል ማድረግ ሀገር አቀፍ ንቅናቄ የጽዳት ዘመቻ በእንጦጦ ፓርክ ውስጥ ተካዷል።
በመርሃ ግብሩ ማስጀመሪያ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የገንዘብ ሚንስቴር ሚንስትር ክቡር አቶ አህመድ ሺዴ በክቡር ጠቅላይ ሚንስትራችን ራዕይና አመራር በሀገራችን ላለፉት 6 አመታት ሰፊውን የህብረተሰብ ክፍሎችን ባሳተፋ መልኩ በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ ዘመቻዎች የሀገራችን የደን ሽፋን እየጨመራ መምጣቱን ገልፃዋሉ። ዘንድሮ እንደከዚህ በፍቱም የህብረተሰቡ ተሳትፎ ከክረምረት በጎ ተግባራት ጋር በማስተሳሰር የተተከሉ ችግኞችን በመንከባከብ አቅማ ደካማ የህብረተሰብ አካለት በመደገፍ ሥራዉ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ መልዕክታቸውን አስተላልፋዋሉ።
ክብርት መሠረት መስቀሌ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተርም በበኩላቸው የአረንጓዴ አሻራ ዓላማን በተመለከተ በዝርዝር መብራሪያ በመስጠት ሥራውም በሁሉም ተቋማት ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል ብለዋሉ።
የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ክብርት ኢንጂነር ለሊሴ ነሜ ሀገር አቀፍ እየተካሄደ ያለውን የሁለተኛ ዙር ፅዱ ኢትዮጵያን ባህል ማድረግ በሚል እየተካሄደ ያለው የአካባቢ ብክለት ማከለከል ንቅናቄ የተመለከተ በዓላማውና ግቦች ላይ ማብራሪያ በመስጠት ሁሉም ግለሰብ፣ ማህበረሰብ፣ የመግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ሁሉ የንቅናቄ አካል በመሆን ፅዱ፣ ንፅህና ለኑሮና ለሥራ ምቹ አካባቢ በመፍጠር የበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ መልክዕታቸውን አስተላልፈዋሉ፡፡
የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄውም ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት በፕላስቲክ ብክለት፣ በአፈርና ውሃ ብክለት ፣በአየር ብክለት፣ በቆሻሻ አያያዝ ፣በድምፅ ብክለትና በአካባቢ ተዕጽኖ ግምገማን መሠረት ያደረገ የህብረተሰብ የግንዛቤ ማስጨበጫ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል ።
የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ዲዳ ድሪባ ባስተላለፉት መልዕክት ለአየር ንብረት ለዉጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚን ለመገንባት መንግስት ስትራቴጂዎችን ነድፎ ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል አንዱ የሆነው የአረንጓዴ አሻራ በመሆኑን የሚተከሉ መንከባከብ ሁሉም የየበኩሉ ኃላፊነት መወጣት እንደሚገባ አንስተው እስካሁን ባከናወናቸው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብሮች እንደ ከተማችንም እንደ ሀገራችንም ተጨባጭ ዉጤቶችን ማስመዝገብ መቻሉን አያይዘው ጠቅሰዋል።