የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ህግ ተግባራዊነት እና የምርት ሽግግርን በተሳካ ሁኔታ ለማድረግ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ትብብር አስፈላጊ መሆኑን ተገለጸ ።
ታህሳስ 14/2018 ዓ.ም
የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ህግ ተግባራዊነት እና አንድ ጊዜ ብቻ አገልግሎት የሚሰጡ የፕላስቲክ ከረጢቶችን መተካት የሚቻልበት፤ የተሳካ የምርት ሽግግር ለመፍጠር ከአምራቾች እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር ለመስረት ውይይት ተካሄደ ። የውይይት መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የአካባቢ ጥበቃ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ኢንጂነር ለሊሴ ነሜ የዜጎች በንጹህ እና ለኑሮ ምቹ በሆነ አካባቢ የመኖር ህግ መንግስታዊ መብትን ለማረጋገጥ መንግስት የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ እንደምትገኝ ገልጸዋል ። በተለይ አፈርን፣ ውሃ እና አየርን በመበከል በሰው ጤና ላይ ጉዳት የሚያደርስ አንድ ጊዜ ብቻ አገልግሎት የሚስጥ ስስ የፕላስቲክ ከረጢቶች ለመከልከል በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጸደቀው የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ አዋጅ ቁጥር 1383/2017 ዓ.ም አንዱ መሆኑን አብራርተዋል ።
ኢንጂነር ሌሊሴ ነሜ አክላም ስስ የፕላስቲክ ከረጢቶች ሳይበሰብሱ ከመቶ አመት በላይ አፈር ውስጥ እንደሚቆዩ ፣ ወደ ማይክሮ ፕላስቲክ በመቀየር የሰው የመተንፈሻ እና የደም ዝውውር ስርዓት ላይ ከፍተኛ የጤና ጉዳት እንደሚያስከትል አብራርተዋል ። አፈርን የሚበክል በመሆኑ አንደ ሀገር በምግብ እራስን ለመቻል እየተሰራ ያለውን ስራ እንደሚጎዳ ተናግረዋል ። እንዲሁም እንስሳትም እየበሉ ሆድ ውስጥ ስለሚቆይ ከእንስሳት የሚገኝ ምርት ስለሚቀንስ ህዝባችን ቅሬታ ማቅረብ መጀመሩን ገልጸዋል ። ጽዱ ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በከተሞች እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎችንም እንደሚጎዳ ገልጸዋል ።በመሆኑም ሁሉም ባለድርሻ አካለት አንድ ጊዜ ብቻ አገልግሎት የሚሰጡ ስስ የፕላስቲክ ከረጢቶች በማህበራዊ እና ኢኮኖሚ ላይ የሚያደርሰው ግምት ውስጥ በማስገባት የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ህግ ተግባራዊነት እና ፕላስቲክ ከረጢቶችን የሚያመርቱ አምራች ወደ አካባቢን የማይበክሉ ምርት እንዲሸጋገሩ በፋይናንስ ፣ በስልጠና ፣ በገበያ ትስስር እና ሌሎች አስፈላጊ ትብብሮችን በማድረግ የምርት ሽግግሩ በተሳካ ሁኔታ እንዲካሄድ ኃላፊነታቸውን መወጣት እንዳለባቸው ተጠይቋል ። የተቋማት አላፊዎችም ለህግ ተግባራዊነት እና ለምርት ሽግግር አስፈላጊ ትብብር እንደሚያደርጉ ቃል ገብቷል ። ጉዳይ የሚመለከታቸው አካለት በሙሉ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ አዋጅ ቁጥር 1383/2017 ዓ.ም ከጥር 23/ 2018 ዓ.ም ጀምሮ አንድ ጊዜ ብቻ አገልግሎት የሚስጥ ስስ የፕላስቲክ ከረጢት ክልከላ እንደሚጀምር አውቀው ከወዲሁ ዝግጂት ማድረግ እንዳለባቸው ተጠይቀዋል ።