የኢ.ፌ.ዲ.ሪ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የሀገር አቀፍ የአካባቢ ብክለት መግቻ ንቅናቄ ውጤትን መሰረት በማድረግ በቀጣይ ከግንዛቤ ሥራዎች ባሻገር የህግ ማስከበር ተግባራትን በትኩረት እንደሚሰራ አስታወቀ።
ጥቅምት 22/2017 ዓ.ም
የውሀ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢ ልማት እና የአካባቢ ጉዳዮች ቋሚ ኪሚቴ ፣ የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አማራሮች፣ የክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ቢሮ ኃላፊዎች፣ የባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና የሥራ ኃለፊዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ በቢሾፍቱ ተካሄዷል፡፡
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ኢንጂነር ለሊሴ ነሜ ተቋሙ በተሰጠው ስልጣንና ኃላፊነት ንፁህና ጤናማ አካባቢን ለትውልድ ለማስረከብ
ከሁሉም ባለድርሻ አካላት፣ ከመላው የማህበረሰብ ክፍሎች እና አጋሮች ጋር በቅንጅት በመስራት የአካባቢ ህግ ተከባሪነትን የማረጋገጥ ሥራ በትኩረት እንሚፈፀም በመግለፅ፡
ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ላለፉት ስድስት ወራት በካሄደው የአካባቢ ብክለት መግቻ ሀገር አቀፍ ግንዛቤ መፍጠሪያ ንቅናቄ ከ 3.5 ሚሊዮን በላይ ለሆነው ህዝብ በቀጥታ መረጃ ተደራሽ በማድረግ ግንዛቤ መፍጠር መቻሉን አስታውሰው የተገኘውን ውጤት ለማስቀጠል የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ከተቋሙ ጋር በቅንጅት መስራት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የ2017 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን፣ ከመድረኩ ተሳታፊዎች የቀረቡ አስተያየቶች ለቀጣይ ሥራ በግብዓትነት የሚወሰዱ ሃሰቦች የተገኘ ሲሆን፡ በንቅናቄውም አመርቂ ውጤት መገኘቱን በመግለፅ የቅንጅታዊ አሰራርን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ውይይት ተደርጎበታል፡፡