የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን የውሃ አዘል መሬትን በቅንጅት ለመጠበቅ ከተለያዩ ባለድርሻ ተቋማት ጋር መግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ ::
ጥር 26/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ
================================
የ28ኛው አለም አቀፍ የውሃ አዘል መሬት ቀን በአለም አቀፍ ደረጀ "Protecting Wetland for common future " በሀገር አቀፍ ደረጀ "የውሃ አዘል መሬትን እናልማ ፣ እንጠብቅ፣ እንከባከብ " በሚል መሪ ቃል ተከበረ ሲሆን፤
ቀኑን በማስመልከት የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክብርት ኢንጂነር ሌሊሴ ነሜ የኢትዮጵያን ብልጽግና በዘላቂነት ለማስቀጠል ውሃ ዋና ሀብታችን በመሆኑ በትኩረት መጠበቅ እንዳለብን በመግለጽ ውሃን ለመጠበቅ የውሃ አዘል መሬቶችን መጠበቅ እና ማልማት ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ጠይቀዋል ።
የውሃ አዘል መሬቶች የውሃማ አካለት ደህንነት ለመጠበቅ፣ የውሃ ብክለትን ለመቀነስ ፣ ጎርፍን ለመከላከል ፣ ሀይቆች እና ወንዞችን በዘላቂነት ለመጠበቅ ፣ የሀገራችን አንዱ የልማት አቅጣጫ የሆነውን የቱሪዝም ልማት ዘላቂነት ለማስቀጠል እና የአየር ንብረት ለውጥን ለመከለከል ያለው ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን አብራርቷል ። ከኮሪደር ልማትና አረንጓዴ አሻራ ጋር ተያይዘው የተሰሩ የወንዞች ዳርቻ ልማት፣ አረንጓዴ እና ንጹህ አካባቢን ለትውልድ ለማስተላለፍ የተሰሩ ስራዎች አበረታች መሆናውን በመግለፅ የተሰሩ ልማቶች በዘላቂነት አገልግሎት እንዲሰጡ እና እንዲስፋፉ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት በቅንጅት በመስራት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል ።
የሚዲያ አካለት የህብረተሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ ሚናቸውን እንዲወጡ ተጠይቀዋል ።
የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 545/2016 አንቀጽ 5/21 የውሃ አዘል መሬቶችን የመቆጣጠር እና ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በቅንጅት ለመስረት በተሰጠው ኃላፊነት ምክንያት በማድረግ ዘላቂ፣ ውጤታማ የውሃ አዘል መሬቶች ልማት ፣ ጥበቃና አጠቃቀም እንዲሰፍን በማድረግ ስነ ምህዳር ለሀገር እድገትና ለሕብረተሰብ ጥቅም እንዲውል ፣ የውሃ አዘል መሬቶችን አጠቃቀም ዙሪያ ያሉ የግንዛቤ ክፍተቶችን በጋራ ለመፍታት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ከስድስት የፌዴራል ዘርፍ መ/ቤቶች ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል ።