የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የ2017 የግማሽ በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምን በማኔጅመንት ደረጃ ውጤታማ መሆኑ ገመገመ፡፡
አዲስ አበባ፣ ጥር 2017 ዓ.ም
======================================
የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የ2017 የግማሽ በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምን በማኔጅመንት ደረጃ ውጤታማ መሆኑ ገመገመ፡፡
በዕቅድ አፈጻጸም የአካባቢ ህግና ደረጃ ተፈጻሚነትና ተተግባሪነት ስርዓት ለማጠናከር የሚያስችሉ የህግ ማዕቀፎችን የማዘጋጀትና አፅድቆ ወደ ተግባር ማስገባት፣ የአካባቢ ሁነታ ዳሰስ ጥናት ማከናወንና ግኝቶችን ተደራሽ ማድረግ፣ ደረቅ ቆሻሻን መልሶ የመጠቀም፣ የአካባቢ ብክለት ደረጃን ለመለየት የናሙና ልኬት አድርግ ህግን የማስከበር፣ የስርዓት ምህዳርና የደህንነተ ህይወት ጥበቃና ቁጥጥር ማድረግ፣ የልማት ፕሮጀክቶች በአካባቢና በማህበረሰብ ተፅዕኖ ግምገማ ስርዓትን ማጠናከር እንዲሁም አለም አቀፍ የአካባቢ ስምምነቶች ትግበራ ክትትል በማድረግ በኩል ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸው ተገምግሟል፡፡
በተለይም በግማሽ በጀት ዓመቱ የ203 ከተሞች የቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ፣ በ139 የፕላስቲክ አምራች ፋብሪካዎች፣ በ671 ናሙና ቦታዎች ላይ የድምፅ ሌኬት እንዲሁም 140 የውሃማ አካላት የናሙና ልኬት በማድረግ የክትትልና የድጋፍ ስራዎች በዘርፉ መካሄዳቸው ተገምግሟል፡፡ በሌላም በኩል የአካባቢ ህግ ተፈጻሚነትና ተተግባሪነትን ከማረጋገጥና እርምጃዎች በመውሰድ በኩል ከ240 ሺህ ሄክታር ውሃማ አካላት ላይ የሚታዩ መጤ ወራሪ ዝርያዎችን የማስወገድ፣ ከ6,500 በላይ ነባር ፕሮጀክቶችን የአካባቢና ማህበረሰብ ተፅዕኖ ግምገማ በማድረግ ይሁንታ መስጠት፣ ለ670 በላይ አማካሩ ባለሙያዎችና ድርጅቶች በአካባቢ ጥበቃ ዘርፍ ሊሰማሩ ላመለከቱ ፍቃድ መስጠት፣ ከ5,600 በላይ አምራች ፋብሪካዎች ላይ በአካል ተገኝቶ ቁጥጥር ማድረግ እንዲሁም ከ500 በላይ ድርጅቶች ተገኝቶ የአደገኛ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ስርዓታቸው በአካል በመገኘት የቁጥጥር እና አስተማሪ እርምጃዎች ተወስዷል፡፡
በአጠቃላይ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከክልል የዘርፉ ቢሮች ጋር የተቀናጀ አሰራር ስርዓትን በመከተል በግማሽ በጀት አመቱ ውጤታ አፈጻጸም መታየቱ በጥንካሬነት ታይቶ በቀሪ ሩብ ዓመቱ የበለጠ ውጤት ለማስገኘት ርብርብ ማድረግ በዋና ዳይሬክተሯ ኢንጂነር ለሊሴ ነሜ አቅጣጫ ተቀምጦ ተጠቃሎል፡፡









