የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን እና የፔፕሲ ካምፓኒ ጋር በጋራ ለመስራት ወይይት አደረጉ፡፡
አዲስ አበባ
መጋቢት 2017ዓ.ም
============
የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂ. ለሊሴ ነሜ ከፔፕሲ ካምፓኒ የአፍሪካ የኮርፖሬት ዳይሬክተር ከሆኑት ከሚስ ሜግና ጋር በዘላቂ የአካባቢ አያያዝ ጉዳይ ላይ የሁለትዮሽ ውይይት አድረገዋል፡፡
የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የደረቅ ቆሻሻን አያያዝ ስርዓትን ላይ የቁጥጥር ስራዎቹን ለማጠናከር ወቅቱ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና አካባቢ ሁኔታ አንጻር የተቃኙ ለማድረግ የሚያስችሉ የህግ ማዕቀፎችን በማዘጋጀትና ለተተግባሪነቱ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን እየሰራ መሆኑ፣ በቀጣይ አንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውሉ የፕላስቲክ ምርቶችን ለማገድ እየተሰራ መሆኑ እንዲሁም በክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የተጀመረውን የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ማፅናትና ባህል ማድረግ ተገቢ መሆኑ ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡
በውይይታቸው ዘላቂ የአካባቢ አያያዝ ጉዳይ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍልን የሚመለከት ጉዳይ መሆኑን በመጥቀስ የግል ሴክተሩ ደግሞ ግንባር ቀደም ሆኖ የማህበራዊ ግዴታውን መወጣት ያለበት መሆኑ፤ በዚህም ረገድ ፔፕሲ የለስላሳ መጠጥ አቅርቦቱን የአካባቢና የማህበረሰብ ተጽዕኖ የቀነሰና የተስማማ ለማድረግ ጥረት እያደረገ መሆን በተለይም የፕላስቲክ ምርት አጠቃቀምን ለመቀነስና በተተኪ ምርት መተካት ብሎም መልሶ ጥቅም ላይ እንዲውል ለማድረግ ከአጋር የቴክኖሎጂ አፍላቂዎች ጋር በመስራት ላይ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡
በማጠቃለያ የአካባቢ ጥበቃ ሴክተር በቀጣይ ስድስት ወራት እንደሀገር “ፅዱ ኢትዩጵያ” በሚል የአካባቢ ብክለት መግቻ ንቅናቄ ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል የትብብር ውይይት አድርገዋል፡፡
====================================
=========================================
የኢፌዲሪ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን
ቀጣዮችን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ