የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በአዲሱ ሀገራዊ የለውጥ እሳቤ ተቋምን በቅንጅት፣ በተነሳሽነት እና በጊዜ የለንም መንፈስ ለመምራት የሚያስችል የአመራሮች አቅም ግንባታ ስልጠና ተጀመረ፡፡
ዛሬ የተጀመረው የአቅም ግንባታ ስልጠና ሲሆን የተለያዩ የአመራርነት ጥበብና የተግባቦት ክህሎት ማሳደጊያ ላይ ያተኮሩ መሆናቸው ተገልጾል፡፡
በአቅም ግንባታ ስልጠናው መክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ኢንጂነር ለሊሴ ነሜ የተዘጋጀው ስልጠና ተቋማዊ የስራ ባህልን በሳይንሳዊ የአመራር ጥበብና ክህሎት በመታገዝ “ዜጎች ጤናማ እና ምቹ በሆነ አካባቢ የመኖር መብታቸውን” እንዲጠበቅላቸው የባለስልጣኑ አመራሮች የመሪነት ሚናቸውን ለመወጣት የሚያስችል ነው፡፡
ክብርት ዋና ዳይሬክተር ተሳታፊዎች የተዘጋጀው ስልጠና ራስን ለአመራርነት ብቁ አድርጎ ሀገራችን
የጀመረችውን የብልፅግና ጉዞ ላይ የሚጠበቅውን የሀላፊነት ሚና ለመወጣት የሚያስችል መሆኑን በመግለጽ በንቃት እንዲሳተፉ በማሳሰብ ስልጠናው በይፋ መጀመሩን አብስረዋል፡፡