የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ሠራተኞች ዓለም አቀፍ የጸረ-ጾታ ጥቃት ቀን እና የሕፃናት ቀንን አከበሩ፡፡
ኅዳር 15/ 2018ዓ.ም
*************************************************************************************************
የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊዎች እና ሰራተኞች በሃገር ዓቀፍ ደረጃ ለ20ኛ ጊዜ የሚከበረውን የፀረ -ጾታዊ ጥቃት ቀንን "ጥቃትን የማይታገስ ማህበረሰብ ለትውልድ ግንባታ"በሚል መሪ መልዕክት እንዲሁም የሕጻናት ቀንን "የሕጻናት ጥበቃ እና የመጫወት መብት ለሁሉም ሕጻናት" የሚል መልዕክት ባነገቡ ሃሳቦች ዙሪያ በተለያዩ መርሃ ግብሮች በዓሉን አክብረዋል፡፡
በዓሉን መልዕክት በማስተላለፍ ያስጀመሩት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ኢንጂነር ለሊሴ ነሜ የሴቶች እና ሕጻናት መብት በአንድ ቀን በሚከበር በዓል ግብ እንደማይመታ በመግለፅ የተሻለው መንገድ የሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ግንዛቤ በማሻሻል በሴቶች እና ሕጻናት ላይ የሚደርሰውን ጥቃት፣መድሎ እና ስነልቦናዊ ጫና በጋራ ለመቅረፍ ርብርብ ማድረግ ተገቢ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ክብርት ኢንጂነር አክለውም በተቋም ደረጃ ለሴቶች ተሳትፎ ልዩ ትኩረት በመስጠት የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ደረጃ በደረጃ ለማሻሻል እንደሚሰራም ተናግረዋል፡፡
የተቋሙ ምክትል ዋና ዳይሪክተር አቶ ንጉሱ ለማ በበኩላቸው በሀገር ዓቀፍ ደረጃ የተያዘውን ሁሉን ዓቀፍ የለውጥ ጉዞ ለስኬት ለማብቃት የሴቶች እና ህጻናት መብቶች ሳይሸራረፉ እንዲተገበሩ ማድረግ አስፈላጊ እንደሆነ በማመን ቁርጠኛ አቋም መያዝ አንዳለበት አሳስበዋል፡፡
የሴቶች እና ሕጻናት ጥቃትን በዘላቂነት ለመከላከል አስቻይ ሁኔታዎች እየተተገበሩ እንደሚገኙ የገለፁት የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ አበባ መጫ በበኩላቸው የሴቶች እና ሕጻናት ጥቃትን የሚከላከሉ ትምህርቶች በዲጂታል ቴክኖሎጂ አማካኝነት በሰፊው መስጠት፣ህጎች መመሪያዎች እና የአሰራር ደንቦች የጸረ ጥቃት እንቅስቃሴዎች ግብ እንዲመቱ በሚያስችል ቁመና ላይ እንዲገኙ ማድረግ፣የህግ ተፈጻሚነት እስከታችኛው መዋቅር ድረስ እንዲሰፍን ማስቻል እና የሕጻናት መብት እና ከለላ ስራዎች በህግ በተቀመጠው አግባብ መሰረት እየተተገበሩ መሆኑን ለመመዘን የቁጥጥር እና ክትትል ስራዎችን እንደሚሰሩ አብራርተዋል፡፡
የዕለቱ መድረክ የሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል ቀጥተኛ ተሳትፎን በማላቅ በሴቶች እና ሕጻናት መብት ጥበቃን ማሻሻል እንደሚቻል የጋራ አቋም ላይ በመድረስ ተጠናቋል፡
====================================
የኢፌዲሪ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን
ቀጣዮችን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ