የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ሠራተኞች በ2017 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ።
ጥቅምት 26 2017 ዓ ም
አዲስ አበባ
==================
የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሠራተኞች እና የበላይ አመራሮች በተቋሙ የመጀመሪያ ሶስት ወራት የሥራ አፈፃፀምን በታቀዱ የትኩረት መስኮችንና አበይት ግቦችን መነሻ በማድረግ የአካባቢ ጥበቃ ቁጥጥርን፣ የኬሚካል ውጋጅ አስተዳደርን፣ የአካባቢ ፍቃድ አሰጣጥን፣ የደህንነተ ሕይወት እና ወራሪ መጤ ዝርያ ቁጥጥርን፣ የኢ ሰርቪስ አገልግሎት አሰጣጥን እና በሌሎች ተግባራት ዕቅድ አፈፃፀም፣ በተገኙ ውጤቶች፣ ባጋጠሙ ተግዳሮቶችና በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን መሠረት ያደረገ የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክብርት ኢንጂነር ለሊሴ ነሜ በመጀመሪያ ሩብ ዓመት የተሻለ ውጤት መገኘቱን በማንሳት በቀጣይ ሩብ ዓመት በአካባቢያዊ የግንዛቤ ትምህርቶች፣ የአካባቢ ህግ ተከባሪነት፣ እየተዘጋጁ የሚገኙ የአካባቢ ህጎች መጠናቅ፣ ከተቋም እስከ ክልሎች ለሚገኙ ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ሥልጠና ማካሄድ እንዲሁም ተቋማዊ የሪፎርም ስራዎች ላይ በትኩረት እንደሚሠራ በውይይቱ ማጠቃለያ ገልፀዋል።
==================================
የኢፌዲሪ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን
ቀጣዮችን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ