የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ማኔጅመንት አባላት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በጋራ ለመስራት እና የሁለትዮሽ የሰራ ግንኙነትን ለማጠናከር የሚያስችል ውይይት አደረጉ፡፡
አዲስ አበባ
=======================================
የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ማኔጅመንት አባላት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በጋራ ለመስራት እና የሁለትዮሽ የሰራ ግንኙነትን ለማጠናከር የሚያስችል ውይይት አደረጉ፡፡
በክብርት ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ለሊሴ ነሜ የተመራው ቡድን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዘዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌና ከፍተኛ አመራሮች ጋር ሁለቱ ተቋማት በአካባቢ ጥበቃና ዘላቂ የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም ዙሪያ የክትትልና የቁጥጥር ስራን ለማጠናከር እንዲቻል በአቅም ግንባታ፣ በጥናትና ምርምር እንዲሁም ሙያዊ ቴክኒክ ድጋፎችን በማጠናከር በሀገር አቀፍና በአለም አቀፍ ደረጃ የተቀመጡ ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት የሚያስችሉ የትብብር ማዕቀፍ ላይ የመነሻ ውይይት አድረገዋል፡፡
የየተቋማቱ ከፍተኛ አመራሮች በአሁን ጊዜ ሀገራችን ኢትዮጵያ እያስመዘገበች ያለውን ፈጣን ልማትና ዕድገትን ዘላቂ በማረጋገጥ በአካባቢና ማህበረሰብ ላይ የሚፈጥረውን ተፅዕኖ በቀነሰ መልኩ እንዲፈፀም ቅንጅታዊ አሰራር ማጠናከር ወቅቱ የሚጠይቀው ጉዳይ መሆኑን አንስተው በጋራ መሰራት አሰፈላጊ መሆኑን አስምረው ተወያይተዋል፡፡
በዚህም የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በህግ የተሰጠውን የአካባቢ ፖሊሲ ትግበራ ክትትልና ቁጥጥር የማድረግ ተልዕኮን ለማገዝ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በአቅም ግንባታ፣ በጥናትና ምርምር እንዲሁም በፈጠራ ሰራዎች ላይ በዘርፉ ያለውን ዕውቅትና ልምድ ለማካፈለና ድጋፍ በማድረግ በአካባቢ ጥበቃ ዘርፍ ወሳኝ ለውጥ ለማስመዝገብ በትብብር እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል፡፡ ይህም የሁለትዮሽ የትብብር ማዕቀፍ አሁን በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመሩ የለውጥና ልማት ስራዎች ከአካባቢ ጋር የተጣጣሙ በማድረግ ዘላቂ ልማት ለማጽናት የተጀመርን የብልፅግና ጉዞ ላይ የራሱ አስተዋፆ እንደሚኖረው በአመራሮቹ ተገልጿል፡፡