የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ተገመገመ ።
ጥቅምት 17/2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ
===============================
የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም የባለስልጣን መ/ቤቱ ኃላፊዎች እና ሰራተኞች በተገኙበት ተገመገመ ።
የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ም/ዋና ዳይሪክተር ወ/ሮ ፍሬነሽ መኩሪያ በበጀት ዓመቱ በመጀመሪያ ሩብ ዓመት የአካባቢ ብክለትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሀገር አቀፍ “ጽዱ ኢትዮጵያን እስከ ባህል ማድረግ” በሚል መሪ ሐሳብ ሁለተኛ ዙር ሀገራዊ ንቅናቄ መጀመሩን እና ሀገራዊ የማስጀመሪያ ፕሮግራም ባለድርሻ አካለት በተገኙበት ንቅናቄ መጀመሩን በመንሳት በንቅናቄውም ለማህበረሰቡና ባለድርሻ አካለት ግንዛቤ ከመፍጠር እና የአካባቢ ህግ ተከባሪነትን ከማረጋገጥ አፃንር ከፍተኛ መሻሻል እየተመዘገበ መሆኑ ገልጸዋል፡፡
መላው የተቋሙ ሠራተኞች በበጀት ዓመቱ የታቀዱ ተግባራት በተቀመጠው ዕቅድ አቅጣጫ መሠረት እንዲሳኩ ለማበረከቱት አስተዋፅኦ በማመስገን የውጤታማነቱን ቀጣይነት ለማረጋገጥ ሁሉም ሠራተኞች መረበረብ እንደሚገበ በመክፈቻ ንግግራቸው አሳስበዋል፡፡
በባለፉት ሶስት ወራት በተለያዩ መደበኛና ማህበራዊ ሚዲያዎች በመጠቀም ከ35.2 ሚሊዮን በላይ እና በገጽ ለገጽ 6.8 ሚሊየን የህብረተሰብ ክፍል ተሳታፊ በመድረግ ግንዛቤ ለማሳደግ መቻሉን፤ የአካባቢና ማህበራዊ ተፅዕኖ ግምገማ ጥናት ሰነዶችን በመገምገም ለ2488 ፕሮጀክቶች የይሁንታ ፈቃድ መስጠት እና የአካባቢ ህግን ከማስከበር አኳያ 319 አምራችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ ህግ የማስከበር ስራ ተሰርቷል፡፡
የክረምት በጎ አድራጎት ሥራን በተመለከተ በሲዳማ ብሔራዊ ክልል መንግስት ደቡበዊ ሲዳማ ዞን ዳራ ወረዳ መጪሾ ቀበሌ የአምስት የአቅመ ደካማ ቤቶችን ለማደስ ውል በመግባት አስፈላጊው ሥራዎች መጀመሩን፤ በደቡብ ምዕረብ ኢትዮጵያ ክልል ቦንጋ ከተማ አስተዳዳር ለአንድ አቅማ ደከማ ቤተሰብ 1 ቤት በማደስ ርክክብ መካሄዱን፤ ለ313 የአቅመ ደካማ ቤተሰብ ተማሪዎች የዓመት ትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉን፤እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ሥር በሚገኘው በአረዳ ክፍለ ከተማ ለሚኖሩ አቅመ ደካማ ለሆኑ ለ50 ነዋሪዎች ለአዲሱ ዓመት የተለያዩ የምግብና የዛይት በማድረግ መዕድ የማጋራት ሥራዎች ተሰርቷል፡፡
በመጨረሻም የግምገማ መድረግ ማጠቃለያ ላይ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ክብርት ኢንጂነር ለሊሴ ነሜ በበኩላቸው በሩብ ዓመቱ ሊተገበሩ ከታቀዱ ዝርዝር ተግባራት አብዛኛዎቹ አመርቂ ውጤት መመዝገባቸውን ጠቅሰው ለቀጣይም ሁሉም ሠራተኞች የተጠለባቸውን ኃለፊነት በቡድን መንፈስ በመስራት የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንዳለባቸው በማሳሰብ በቀጣይ ሩብ ዓመት የሚሰሩ የትክረት አቅጣጨዎችን ሰጥተዋል፡፡

