የኢ.ፌ.ዲ.ሪ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን የ2018 የአለም አካባቢ ቀንን ከአዲስ አበባ፣ ከኦሮሚያ ፣ ከተለያዩ አለም አቀፍና ሀገር በቀል ድርጅቶች ፣ ከፌዴራልና ከክልሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በእንጦጦ ፓርኪ የተሰራውን የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች ጉብኝት በማድረግ እና በተለያዩ ኩነቶች በደመቀ ሁኔታ አከበረ።
ክብርት ዶ/ር ለሊሴ ነሜ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ባስተላለፉት መልዕክት የአካባቢ ሃብት ምትክ የለሽ መሆኑን በመረዳት አካባቢን ሣይንሥ በሆነ መንገድ ለመጠበቅ፣ ለማልማት እና ለመንከባከብ የሚያሥችሉ አዋጆችን፣ ደንቦችን፣ መመሪያዎችን እንዲሁም ዘላቂ የአካባቢ ሃብት አጠቃቀም ሥርዓትን በመዘርጋት በሁሉም ደረጃ ውጤታማ ሥራዎች ለማከናወን ተችሏል።
ለዚህም በእንጦጦ ፖርክ መንግሥት በልዩ ትኩረት ከሠራቸው የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች በአንድ ሺህ ሰላሣ ሰባት ሔክታር ውስጥ በሀገር በቀል በሆነ እውቀት በኮንሶ ቪሌጅ የተሰራ ሥራ ማሰያ እንደሆነ ገልጸዋሉ።
የእንጦጦ ፖርክ ስራ ዜጎች አብረው በራስ ዕውቀት እና ካፒታል በተቀላጠፈ አፈፃፀም ሌሎች የልማት ትሩፉት ስራዎችን መሥራት እንደሚችሉ ሕያው ማሳያ መሆኑን በመንሳት በዕለቱ ለአካባቢ ጥበቃ ጉልህ አስተዋፅኦ እያበረከቱ የሚገኙት የኮሪደር ልማት፣ የወንዝ ዳርቻ ስራዎች፣ እና የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ተጠናክረው እንዲሁም በየክልሉ ተሥፉፍተው እንደሚሰሩ በመግለፅ ይህም በክቡር ዶ/ር አቢይ አህመድ አመራር ሰጪነት የሚሰሩ የአረንጓዴ ኢኒሼቲቭ ስራዎች በሀገር ደረጃ ውጤታማ ሥራዎችን መሰራታቸውን አንስተዋሉ፡፡
የዕንጦጦ ፖርክ ስራ ዜጎች አብረው በራስ ዕውቀት እና ካፒታል በተቀላጠፈ አፈፃፀም ሌሎች የልማት ትሩፉት ስራዎችን መሥራት እንደሚችሉ ሕያው ማሳያ መሆኑን በአፅዕኖት ገልፀዋለ።
የፕላን እና ልማት ሚኒሥቴር ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር አቶ በረከት ተሥፋ ፂዎን በበኩላቸው በጉብኝቱ የታየው የፅዱ ኢትዮጵያ ሥራ ውጤት ማሳያ መሆኑን በመግለፅ በቀጣይም የአረንጓዴ ኢኮኖሚ መሰረት የሚሆኑ መሰል ስራዎች እንደሚሰሩ ተናግረዋል። የተቀናጁ፣ኢኮኖሚያዊ ፋይዳቸው የላቀና ለዘመኑ የአየር ንብረት ለውጥ ተግዳሮት ምላሽ ሰጪ መሆናቸውን ተናግረዋል።
የዓለም የአካባቢ ቀንን አስመልክቶ ዛሬ በተካሔደው የመሥክ ጉብኝት የተሳተፉ የተቋማት ተወካዮች እና ሰራተኞች በጉብኝቱ መደሰታቸውን የገለፁ ሲሆን አካባቢን መጠበቅ እና ማልማት ፈርጀ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው በተግባር መማራቸውን ገልፀዋል።
ከተሳታፊዎቹም መካከል የተባበሩት መንግሥታት የአካባቢ ፕሮግራም ዳይሬክተር ዶ/ር ማርጋሬት ኦዱክ በጉብኝቱ መደሠታቸውን ገልፀው በእንጦጦ ደን እና በተፋሰሡ የተፈጥሮን ፀጋ፣ የማህበረሰብ ነባር ዕውቀትን ከዘመኑ ሣይንስ ጋር ተዋሕዶ የተሠራው የአካባቢ ልማት ሥራ እጅግ እንዳስደነቃቸው ተናግረዋል። ሥራው የአካባቢውን ማህበረሰብ ባሳተፈ መልኩ መሰራቱ ከአካባቢ ጥበቃ መሰረታዊ መርሕ ጋር ስምሙ ያደርገዋል ሲሉ ዳይሬክተሯ ተናግረዋል።
የዓለም የአካባቢ ቀንን በአልን አስመልክቶ ዛሬ በተካሔደው የመሥክ ጉብኝት የተሳተፉ የተቋማት ተወካዮች እና ሰራተኞች በጉብኝቱ መደሰታቸውን የገለፁ ሲሆን አካባቢን መጠበቅ እና ማልማት ፈርጀ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው በተግባር መማራቸውን ገልፀዋል።
በጉብኝቱ ሐገር በቀል ዛፎች ሥላላቸው ዓይነተ ብዙ ጠቀሜታ፣ ከደን ልማት ጋር ቅይጥ ግብርና በማካሔድ ሥለተገኙ የፍራፍሬና ማር ምርት ውጤቶች፣ እንዲሁም የኤኮ ቱሪዝም ፋይዳን መገንዘብ ተችላል።
በዓለም ለ53ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ33ኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘው የአካባቢ ቀን "ክላይሜት አክሽን" በሚል መሪ ሃሳብ በቀጣይ የአካባቢ ልማት ውጤቶችን በማሳወቅ እና ማኅበራዊ ተሳትፎን በማነቃቃት ይቀጥላል።በዕለቱ የተካሔደውን ጉብኝት የፌዴራል እና የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ኃላፊ እና ሰራተኞች፣ የተባበሩት መንግሥታት የአካባቢ ፕሮግራም ዳይሬክተር፣ የፕላን እና ልማት ሚኒሥቴር ሚኒስትር ዲኤታ የከንቲባ ቢሮ ተወካዮች እንዲሁም የተለያዩ አለማቀፍ ተቋማት ተወካዮች ተሳትፈዋል ።