የአካባቢ ጥበቃ ስራን ውጤታማ ለማድረግ እና ፅዱ ኢትዮጵያን ለትውልድ ለማስተላለፍ የሚዲያና የኮሙኒኬሽን ስራ የጎላ ሚና መኖሩ ተገለፀ::
መጋቢት 19/2017ዓ.ም
""""""""""""""""""""@""""""""""""""""""
የአካባቢ ጥበቃ ስራን ውጤታማ ለማድረግ እና ፅዱ ኢትዮጵያን ለትውልድ ለማስተላለፍ የሚዲያና የኮሙኒኬሽን ስራ ጉልህ ሚና እንደሚጫወት የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክብርት ኢንጅነር ለሊሴ ነሜ ባለስልጣኑ ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) ጋር በካሄደው በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት በተፈራረሙበት ወቅት ገልፃዋሉ።
በተለይም የአካባቢ ጉዳይን ለማህበረሰቡ ግንዛቤ ከመፍጠር ረገድ ጉልህ ሚና እንዳለው በመግለፅ ለኢትዮጵያ ምሳሌ ከሆነው ኢቢሲ ጋር መስራት አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚቻልም ግልፀ መልዕክት አስተላልፈዋሉ።
ስምምነቱ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ በሁለተኛ ዙር ፅዱ ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ ሀገራዊ ንቅናቄ ለሚቀጥለው ስድስት ወራት ለማሳካት የተቀመጡ ግቦችን ፤ የህዝብ ንቅናቄ፣ የህግ ማስከበር ስራን የማረጋገጥ ፣ በትምህርትና ግንዛቤ በመፍጠር የአካባቢ ጥበቃ ሰራዎችን አጠናክሮ የመስራት እንዲሁም አካባቢ ጥበቃን መሰረት ያደረገ ፕሮግራምን መስራትን የሚያካትት ነው።
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ስራ አስፈፃሚ አቶ ጌትነት ታደሰ በበኩላቸው የአካባቢ ጥበቃ ጉዳይ የአገር ግንባታ ጉዳይ መሆኑንና በተለይም በክቡር ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ መሪነት የአረንጓዴ አሻራ እንደ ሀገር ምሳሌ መሆን መቻሉን በመግለፅ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በአዋጅ የተሰጠውን ስልጣን ውጤታማ ለማድረግ ሁለቱም ተቋማት የያዙትን የአገር ግንባታ ስራ በጋራ ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት መሆኑን በመግለፅ አሰፈለጊው የሚዲያና ኮሙኑኬሽን ስራ እንደሚሰራ ገልፀዋል።
=========================================
የኢፌዲሪ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን
ቀጣዮችን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ