የአካባቢ ብክለትን መግታትና መቆጣጠር በሴቶች ላይ የሚደርሰውን የተጋላጭነት ተፅዕኖ እንደሚቀንስ ተገለፀ።
ታህሳስ 11/2017ዓ.ም
ቢሾፍቱ
የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክብርት ኢንጂነር ለሊሴ ነሜ በአለምአቀፍ ደረጃ ለ33ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ19ኛ ጊዜ የሚከበረውን የነጭ ሪቫን ቀን በተቋም ደረጃ በተከበረበት ወቅት እንደገለፁት በአካባቢ ብክለት ይበልጥ ተጋላጮች ሴቶች መሆናቸውን በመግለፅ ችግሩን ለመፍታት ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን እንዲሁም የሴቶች ተጠቃሚነት እና ተሳታፊነትን በማጠናከር ረገድ በጋራ መሰራት እንዳለበት ጠቁመው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ተፅእኖ ፈጣሪ ተቋም እንዲሆን ትውልድ ላይ የሚጣል አሻራ ለመጣል አስፈላጊውን የህግ ተከባሪነት ማስከበር ስራዎች በቅንጅት መሰራት እንዳለበት
መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።
የባለስልጣኑ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካትቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባ መጫ በበኩላቸው ለነጭ ሪቫን ቀን መታሰብ ምክንያት የሆነው በሴቶች ላይ የተፈፀመ ጅምላ ጭፍጨፋ መሆኑን በማስታወስ ፀረ ሴቶች ጥቃትን ለመከላከል ሴቶችን በኢኮኖሚ አቅም ማሳደግ እንዲሁም ፆታዊ ጥቃትን የሚያበረታቱ አስተሳሰቦችና ድርጊቶችን በጋራ መታገል እንደሚገባ ገልፀው በዓሉ"የሴቷ ጥቃት የኔም ነው ዝም አልልም "በሚል መሪ ቃል እየተከበረ እንደሚገኝ ገልፀዋል ።
በበዓሉ ላይ የባለስልጣኑ ሴት ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ትርሐስ መብራቱ በአንጓዴ ቴክኖሎጂ ተፅእኖ ፈጣሪ ሴት በሚል ዘርፍ ሽልማት መግኘታቸውን በመግለፅ ይህም ለተቋሙ እምርታን የሚጨምር መሆኑንና ተሞክሮዎች የማስፋት ስራዎች መሰራት እንደሚጠበቅ ተገልጿል።
በመጨረሻም በባለስልጣኑ የሚተገበሩና በሴቶች ተጠቃሚነት ላይ ትኩረት በመስጠት ሴቶችን ተጠቃሚ ያደረጉ ፕሮጀክቶች ስራዎች ቀርበዋል።
በበዓሉ ላይ የተቋሙ የበላይ ኃላፊዎች ፣ የተቋሙ ሴት ሰራተኞች እንዲሁም ወንዶች ተሳትፈዋል ።
==================================
የኢፌዲሪ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን
ቀጣዮችን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ