"የፅዱ ኢትዮጵያን ባህል ማድረግ" ንቅናቄን በአካባቢ ህግ ተከባሪነት አረንጓዴ ሰርተፍኬት (Compliance Green Certification) አሰጣጥ ስርዓት ዝርጋታ ለመመልከት የመስክ በአምራች ኢንዱስትሪው ጉብኝት ለማድረግ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክትር ክብረት ወ/ሮ ፍሬነሽ መኩሪያ እና የማኔጅመንት አባል በኢትዮ ሌዘር ኢንዱስትሪ ኃ.የተ.የግ.ማ አዋሽ ቆዳ ፋብሪካ በመገኘት የህግ ተከባሪነት አረንጓዴ ሰርተፍኬት (Compliance Green Certification) የአተገባበር ሥርዓትን ለማረጋገጥ የመስክ ጉብኝት አድርገዋል፡፡
የመስክ ጉብኝቱ ዋና ዓላማ የነበረው በ2016 ዓ.ም ያወጣውን የህግ ተከባሪነት አረንጓዴ ሰርተፍኬት መስፈርቶች ማለትም የኬሚካል አያያዝ እና ማከማቸትሥርዐት፤ የፍሳሽ ቆሻሻ አያየዝ ፣አየር ብክለት፣ ድምፅ ፣ ጨረር፣ ሙቀት እና ንዝረት ብከለቶች፣ የደርቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ የአካባቢና የሥራ ላይ ደህንነት ጠንቅ ግምገማ ሥርዐት፤ የሥራ አካባቢ ጤና፣ የአደጋና የአስቸኳይ ጊዜ ሥርዐት፤ የአካባቢ ፖላሲና ዕቅድ ዝግጅት እና የመረጃ አያያዝ ስርዓት እና በአካባቢያዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ለሠራተኞች የክህሎት እና ግንዛቤ ማጎልበቻ ሥልጠና መሰረት በማድረግ አዋሽ ቆዳ ፋብሪካ ያለበትን ደረጃ በመገምገም ደረጃውን ማስቀመጥ ነበር፡፡
በመስክ ጉብኝቱ ግምገማ መሰረት ድርጅቱ ከላይ የጠቀሱትን አብዛኛውን መስፈርቶችን ያሟላ ሲሆን በውስንነት የታዩትን ስራዎች ለምሳሌ ወቅቱን የጠበቀ የአካባቢ ኦዲት ለአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ሪፖርት አለማቅረብ እና የአካባቢ ንፅህና እና የስራ ላይ ደህንነት መጠበቂያ ቁሳቁስ የተሟላ ብሆንም አጠቃቀም ላይ አነስተኛ ክፍተት መኖሩን የመስክ ጉብኝቱ ቡድን ተመልክቶ ግብረመልስ የሰጠ ሲሆን ቀሪ የማሻሽያ ሰራዎችን በመስራት ለሌሎች መስል ድርጅቶች ተሞክሮ ሊሆን እንደሚችል አስተያየት በመስጠት የመስክ ጉብኝቱ ተጠናቋል፡፡
ይህም የመስክ ላይ ክትትልና ቁጥጥር ስራ ለፅዱ ኢትዮጵያን ባህል ማድረግ ንቅናቄ በአምራች ኢንዱስትሪው ባህል ለማድረግ በስታንዳርድ መሰረት ለሚያመርቱ የአረንጓዴ ሰርተፍኬት እውቅና የሚሰጥ ዘላቂ የአካባቢ አያያዝ ስርዓትን የሚያጎለብት አሰራር ነው።

