የአካባቢና የአየር ንብረት ለውጥ የህልውና እና የልማት ጉዳይ ሆኖ በህገ- መንግስት እና የሀገሪቱ መሪ እቅድ አካል ውስጥ ተካቶ እየተሰራ መሆኑን ተገለጸ ።
ጥር 21/2018 ዓ.ም
አርባ ምንጭ
፨፧፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ሀገር አቀፍ የ2018 ዓ.ም የአካባቢ ጥበቃ እና የአየር ንብረት ለውጥ የስድስት ወር የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክን በንግግር ያስጀመሩት የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ስዩም መኮንን ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ማጣጣም ፣ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ እና የአካባቢ ጥበቃን የህልውና እና የልማት ጉዳይ አድርጋ በመውሰድ በህገ-መንግስት ጭምር እውቅና ሰጥታ እየሰራች እንደምትገኝ ገልጸዋል ።የለውጡ መንግስት ባለፉት ሰባት ዓመታት ለዘርፉ የሰጠው ትክረት እና የማያቋርጥ ተግባር የመንግስት ቁርጠኝነትን የሚያሳይ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው እንዲሁም የአስር ዓመት መሪ እቅድ ውስጥ ካሉ አበይት ምሶሶ አንዱ ሆነው እየተተገበረ እንደሚገኝ ተናግረዋል ።
የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፍሬነሽ መኩሪያ እንዳሉት፤ ዜጎች ንጽህና ደህንነቱ በተጠበቀ አካባቢ የመኖር መብታቸው እንዲጠበቅ የአካባቢ ስራ በዘላቂ ተጠናክሮ መሰረት ይገባል ብለዋል።በአገሪቱ ባለፉት ጊዜያት የተጀመሩ የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች የአገሪቱን የመፈጸም አቅም ያመላከቱ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚወሱ መሆናቸውን ያብራሩት ምክትል ዋና ዳይሬክተሯ፤ በዘርፉ ተጨባጭ ለውጦች እንዲመዘገቡ የሚያግዙ የተለያዩ የሕግ ማዕቀፎች ወጥተው በመተግበር ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።በተለይ በጠቅላይ ሚንስቴር በክቡር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የተጀመሩት የአረንጓዴ አሻራ ፣ የኮሪደር ልማት፣ የወንዞች ዳርቻ ልማት እና ጽዱ ኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ስራ ጋር በከፍተኛ ሁኔታ የሚደጋገፉ በመሆናቸው በዘርፉ ለውጥ መምጣቱን አብራርተዋል ። የመድረኩ ተሳታፊዎችም የጽዱ ኢትዮጵያ የህዝብ ንቅናቄ በመሰረቱ ተጨባጭ ለውጥ እየመጣ በመሆኑ በማንሳት በቀጣይም የህዝቡን ግንዛቤ ለማሳደግ የሚሰሩ ስራዎች ተጠናከሮ መቀጠል እንዳለባቸው ጠይቀዋል ።
በመድረኩ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎችን ጨምሮ የፌዴራል ፣ የሁለቱ ከተማ አስተዳደር እና የሁሉም ክልሎች የአካባቢ ጥበቃ ዘርፍ አመራሮች ተሣታፊ ናቸው።
====================================
የኢፌዲሪ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን
ቀጣዮችን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ