የአረንጓዴ አሻራ፣ የፅዱ አካባቢን እንዲሁም አካባቢ ጥበቃ ስራ ባህል ሆኖ ለቀጣይ ትውልድ መተላለፍ እንዳለበት ተገለጸ ።
የካቲት 21/2017 ዓ.ም
ጅማ
================
የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና የዳይሬክተር ኢንጂነር ሌሊሴ ነሜ ሀገራችን ውብ ፣ ጽዱና አረንጓዴ ሆኖ ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ የአረንጓዴ አሻራ የልማት ስራዎችን ባህል አርገን ለተተኪው ትውልድ ማስተላለፍ አለብን ብለዋል።
ይህን
የተናገሩት በጅማ ከተማ እየተካሄደ ባለው ሀገር አቀፍ የአካባቢ ጥበቃ ዘርፍ
የሰባት ወራት የእቅድ አፈጻጸም የግምገማ መድረክ ላይ ነው።
ኢንጂነር ሌሊሴ የአየር ብክለትን ለመከላከል ፣ የውሃ አዘል መሬት እንክብካቤ እና የሙቀት ሳቢ ጋዞች ልቀትን ልኬት እና ቁጥጥር ከሌሎች ተቋማት ጋር የቅንጀት አሰራር ስምምነት ዘርግቶ እየተሰሩ መሆኑን ፣ የአካባቢ እና የደህነተ ህይወት ላብራቶሪ እየተቋቋመ መሆኑን፣ አንድ ግዜ ጥቅም የሚሰጡ የፕላስቲክ ውጤቶችን ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ለመከለከል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ፣ አደገኛ ቆሻሻና ኬሚካሎች ሀገር ውስጥ ለማስወገድ የሚያስችል መሰረተ ልማት ለመገንባት ጥናት እየተደረገ መሆኑን ፣ የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል የህዝብ ተሳትፈው ለማሳደግ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች መፈጠሩን እና የአካባቢ ህግና ደረጃዎችን የተላለፉ ተቋማት ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን እንዲሁም በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። ለአካባቢ ጥበቃ አስተዋጽኦ ያላቸውን በጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ የተጀመሩትን የአረንጓዴ አሻራ፣ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች፣ የኮሪደር ልማት እና ጽዱ ኢትዮጵያ የልማት ስራዎችን በሁለተኛው የብልፅግና ጉባዔ ትኩረት መሰጠቱን ተገልጸዋል ።
በኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውሃ ፣ የመስኖ ፣ ቆላማ አካባቢ እና የአካባቢ ልማት ቋሚ ኮሚቴ አባል የተከበሩ አቶ ካሊድ አባመጫ ሐጂ እንደ ሀገር በአካባቢ ጥበቃ ዘርፍ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች አበረታች እና መልካም ጅምሮች መኖራቸውን ገልጸው፣ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ እና የልማት ተቋማት የህግ ተከባሪነት አሁንም በትኩረት ክትትል ቁጥጥር እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል ።
በግምገማ መድረኩ ላይ በኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውሃ ፣ የመስኖ ፣ ቆላማ አካባቢ እና የአካባቢ ልማት ቋሚ ኮሚቴ አባላት ፣ ከኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አመራሮች እና የክልል እና የከተማ መስተዳደሮች የአካባቢ ጥበቃ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል ።