የተቀናጀ የቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ ሥርዓት ማስፈንን አላማ ያደረገ የተማሪዎች ጥያቄ እና መልሥ ውድድር ተጀመረ
ኅዳር 23 2018 ዓም
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን በክቡር ጠ/ሚኒሥትር አነሳሽነት የተጀመረውን የፅዳት እና የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች ከዘመቻነት ወደ ማህበረሰብ ባሕልነት እንዲሸጋገር የተደራጀ ተግባራትን አያከናወነ ይገኛል፤ ዛሬ የዚሁ ተግባር አካል የሆነው እና የተቀናጀ የቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ ሥርዓትን መሰረት ያደረገ የተማሪዎች የጥያቄ እና መልስ ውድድር በአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ፪ኛ ደረጃ ት/ቤት ተጀመረ።
በአስራ ሶሥት ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች እና ሃያ ሶስት አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶችን አካቶ የሚካሔደው የጥያቄ እና መልሥ ውድድር ዋነኛ ዓላማ ተማሪዎች የተቀናጀ የቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ ምንነትን ተረድተው በሀገራቀፍ ደረጃ እየተካሔደ ለሚገኘው የፅዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ማስቻል ነው።
በተማሪዎች የጥያቄ እና መልስ ውድድር ላይ በመገኘት መልዕክታቸውን ያስተላለፋት የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሪክተር ክብርት ኢንጂነር ለልሴ ነሜ ሲሆኑ በመልዕክታቸውም፤ ' ሁሉም ተማሪዎች የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች ምንነትን በመገንዘብ በሀገር ዓቀፍ ደረጃ እየተካሔደ በሚገኘው የፅዱ ኢትዮጽያ ንቅናቄ የነቃ ተሳትፎ እንድታደርጉ ' በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ክብርት ኢንጂነር አክለውም ከቀጣይ ታህሳስ ወር ጀምሮ የስስ ፕላስቲክ ከረጢት ጥቅም ላይ መዋሉ እንደሚያከትም በማስታወስ ተማሪዎች በተኪ ምርት የመገበያየት ልምምድ እዲያዳብሩም አሳስበዋል።
ዋና ጭብጡን በቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ እንዲሁም በፕላስቲክ ብክለት ጠንቆች ዙሪያ ያደረገው የተማሪዎች የጥያቄ እና መልስ ውድድር በአዲስ አበባ ከተማ በአዲስ ከተማ ፪ኛ ደረጃ ተማሪዎች መካከል ተካሒዳል። በውድድሩም ብልጫ ላሳዩ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማቶች ተሰጥቷል።
በተማሪዎች መካከል የሚካሔደው የጥያቄ እና መልስ ውድድር በቀጣይ በተለያዩ ት/ቤቶች በሚገኙ ተማሪዎች መካከል እንደሚካሔድ ከመድረክ ተገልፃል።
====================================