ሃገረችን ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ 2027 ዓ.ም የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የአካባቢ ቀን ለማስተናገድ ለተበበሩት መንግስታት የአካባቢ መርሀ ግብር (UNEP) በይፋ ጥያቄ አቅርባለች። በዓሉ እውን ይሆን ዘንድ የተሟላ ዝግጅት ታደርጋለች። ሃገራችን በአካባቢ ጉዳዮች -
አረንጓዴ ሌጋሲ፣ የኮሪደር ልማት፣ የወንዝ ዳርቻ ልማት፣ ጽዱ ኢትዮጵያን ባህል ማድረግ የህዝብ ንቅናቄ በመተግበር እንዲሁም የአካባቢ የህግ ማእቀፍ በማዘጋጀትእና በመተግበር ተምሳሌታዊ ናት። ለዚህም ማሳያ በአካባቢና በጤና ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ያለውን ፕላስቲክ ብክለትን ለመከላከል - ለአንድ ጊዜ ቢቻ አገልግሎት ላይ የሚውል ፕላስቲክ ምርት እንዳይመረት እና ጥቅም ላይ እንዳይውል የሚከለክል እንዲሁም የስነ ምህዳር አገልግሎት ክፍያ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችሉ አዋጆችን በማጥትና በመተግበር ላይ ትገኛለች። ሃገራችን አካባቢ አያያዝ ጉዳይ ላይ በተምሳሌትነት የምትጠቀስ ብቻ ሳትሆን፣ ትላልቅ ዓለም አቀፍና አህጉራዊ ስብሰባዎች በማስተናገድ ትልቅ ተሞክሮ ያላት ሃገር እና ብዙ ሃገራት የመሰከሩላት ናት።
====================================
የኢፌዲሪ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን
ቀጣዮችን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ