ኢትዮጵያ በአካባቢ ጥበቃ በዘርፉ የተሻላ ስራ ለሰሩ ተቋማት እና ግለሰቦች የእውቅና ሽልማት ተሰጠ
ግንቦት 28/2017 ዓ.ም
""""""""""""""""""""@"""""""'"''''''''''''""
ሁለተኛ ዙር የብክለት ቅነሳ ንቅናቄ ማስጀመሪያ ምክንያት በማድረግ በአካባቢ ጥበቃ የተሻላ ስራ ለሰሩ ተቋማት እና ግለሰቦች የእውቅና ሽልማት ተሰጠ።
የእውቅና ሽልማት የተሰጣቸው ተቋማት እና ግለሰቦች :_
1ኛ. ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ በወንዝ ዳርቻ ልማት ፣በቆሻሻ አወጋገድ ፣በአረንጓዴ አሻራ ፣ የህዝብ መዝናኛ ፓርኮች፣ የጭስ አልባ ትራንስፖርት መሰረተ ልማት መስፋፋት እና በአጠቃላይ ጽዱና ለኑሮ ምቹ የሆኑ አካባቢን ከመፍጠር አንፃር ለሰሩት አርአያ የሆነ የተሻለ ውጤት፣ ላሰዩት ብቃት ያለው አመራርና ላስመዘገቡ ውጤት ፣
2ኛ. የትራንስፖርትና በሎጂስቲክ ሚኒስቴር
ጭስ አልባ ትራንስፖርት እና መሠረተ ልማት በማስፋፋት፣ አካባቢን የሚበክሉ አሮጌ መኪኖች ወደ ሀገር እንዳይገቡ የተሰራው ስራ ፣አካባቢን የማይበክሉ ቴክኖሎጂዎችን በማስፋፋት
3ኛ. የአለም ሎሬት ዶክተር ተወልደ ብርሃን
ገ/ እግዚአብሔር
የአካባቢ ጥበቃ እና የብዘሐ ህይወት ኢንስቲትዩት መስራች ፣ የሙቀት አማቂ ጋዞችን ለመቀነስ አፍሪካን ወክለው በአለም መድረክ የመሞገት እና የመደራደር ስራዎች እና ብዙ ዘርፉን በሚመለከት ብዙ ጥናታዊ ጽሁፍ የሰሩ ሳይንቲስት በመሆናቸው
4ኛ .የኢትዮ ቴሌኮም
የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ህብረተሰቡን ግንዛቤ ለማስጨበጥ ባደረጉት ትብብር፣ ዲጅታል ኢኮኖሚን ለመገንባት በተሰራው ስራ ፣ጭስ አልባ ትራንስፖርትን ለማስፋፋትን የተሰራው ስርዓት ወዘተ
5ኛ. የኢትዮጵያ አየር መንገድ
ዘላቂ የአካባቢ ስርዓት በመገንባት ፣ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ እና ምቹ የስራ አካባቢን ከመፍጠር በተሰሩ ስራዎች የእውቅናና ሽልማት ቀኑ የክብር እንግዳ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልግና ፓርቲ ም/ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ እጅ ተቀብለዋል ።

====================================
የኢፌዲሪ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን
ቀጣዮችን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ