በኢትዮጵያ የሚገነባው አዲስ ሀገራዊ ትርክት ዜጎች በወንድማማችነትና እህታማማችነት ለሀገራቸው እድገትና ልማት በጋራ አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ የሚረዳ መሆኑን ተገለጸ ።
=============================
በኢትዮጵያ የሚገነባው አዲስ ሀገራዊ ትርክት ዜጎች በወንድማማችነትና እህታማማችነት ለሀገራቸው እድገትና ልማት በጋራ አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ የሚረዳና ላለፉት 7 የለውጥ ዓመታት የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ስብራቶቿ ከመሠረቱ የመጠገን አስተማማኝ ሂደት ውስጥ በመግባት በሁሉም ዘርፎች ተጨባጭ ለውጦች የተመዘገቡበት መሆኑን ገለጸ።
የፕላና ልማት ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመተባበር ሀገራዊ ለውጥና ተቋማዊ ሪፎርሞች የተበሰሩበትን የመጋቢት 24/ 2010 ዓ.ም ሰባተኛ ዓመት ዝክረ በዓል ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው የሠራተኞች ውይይት መድረክ ላይ በፕላንና ልማት ሚኒስትር ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት ክቡር አቶ ስዩም መኮንን ባስተላለፉት መልዕክት ነው።
ባለፉት 7 አመታት በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማህበራዊ ዘርፎች የተካሄዱ ተጨባጭ ለውጦችን በጥልቀትና በስፋት ያብራሩት አቶ ስዩም፤ ከእነዚህ መካከልም በመጠፋፋትና በመገፋፋት ላይ የተመሰረተውን ኋላ ቀር የፖለቲካ አስተሳሰብና ስብራት መጠገን የሚችል ብሄራዊ ትርክት መገንባት ተችሏል ብለዋል።
ባለፉት 60 አመታተ የነበረው ኋላ ቀር የፖለቲካ ባህላችንም ሀገሪቱን ብዙ ዋጋ ሲያሰከፍላት መቆየቱን አውስተዋል።
ሌላው የፖለቲካ ስብራትን ከመጠገን አኳያ ከተወሰዱ እርምጃዎች መካከል አካታችነት ሲሆን የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በኢትዮዽያ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚባል ደረጃ በማዕከላዊ ፖለቲካ ውስጥ እንዲሳተፉ የተደረገበት አዲስ የፖለቲካ ባህል መሆኑንም ተጠቅሷል።
የቆዩ ቅራኔዎችና አለመግባባቶች በምክክርና በውይይት ልዩነቶችን ለመፍታት ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን መቋቋሙንም ሌላው የፖለቲካ ስብራትን ለማከም ከተወሰዱ እርምጃዎች መካከል አንዱ መሆኑ ተነግሯል።
የዲሞክራሲ ተቋማትን በማጠናከር ረገድ የሰባዊ መብት ኮሚሽን፣ ምርጫ ቦርድንና የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቃም ነጻና ገለልተኛ ሆነው እንዲሰሩ ጠንካራ እርምጃዎች መወሰዳቸውን አንስተዋል።
በኢኮኖሚው ዘርፍም ሰፋፊ ስራዎች ተሰርተዋል ያሉት ክቡር አቶ ስዩም በግብርናው ዘርፍ በተለይም በስንዴ ምርት አመርቂ ስራ ተሰርቷል። በዚህም በስንዴ ምርት ራስን ከመቻል አልፎ በኢትዮዽያ ለመጀመሪያ ጊዜ ስንዴ ወደ ውጭ መላክ ችላለች ብለዋል።
በቱሪዝም እና በማዕድን ዘርፍም የውጭ ምንዛሬ እንዲያስገኙ ባለፉት 7 ዓመታት ብዙ ስራዎች መሰረታቸውን ክቡር አቶ ስዩም ገልጸዋል።
በማህበራዊ ልማት በኩልም በከተማ ልማት በኩል እንደ ኮሪደር ልማት ያሉ ፕሮጄክቶች ዜጎች ውብና ጽዱ ኑሮ እንዲኖሩ ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን አብረርተዋል፤ ይህም ወደ ሀገሪቱ የገጠር አካበባዎችም እየተስፋፋ ይገኛል ተብሏል።
ይሁን እንጂ እነዚህ ለውጦች የተመዘገቡት በከባድ ፈተናዎች ውስጥ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው አብራርተዋል። ከፈተናዎች መካከልም የኮሮና ወረረሽኝና የሰሜኑ ጦርነት በሀገሪቱ ላይ ከባድ ጫና ማሳደራቸውን ጨምረው ገዕጸዋል።
የተመዘገቡ አበይት ለውጦችንና የተሻለ ለውጥ ለማስመዝገብ ሁለም በትጋትና በንቃት እንዲሰራ ክቡር አቶ ስዩም አሳሰበዋል።
በሌላ በኩል ዝክረ በዓሉን በማስመልከት የተዘጋጀውን ሀገራዊና የዘርፍ የሰባት ዓመታት ዋና ዋና የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊና የፖለቲካ ትሩፋቶችን፣ ተግዳሮቶችና የወደፊት አቅጣጫዎችን የሚዳስስ ጽሑፍ ላይ ሰፊ ውይይት ተካሄዷል ።
====================
=========================================
የኢፌዲሪ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን
ቀጣዮችን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ