በሥነ-ምግባር ላይ የተመሠረተ የአመራር ሥርዓትን ለማሥፈን ያለመ ሥልጠና ለከፍተኛ አመራሮች እየተሰጠ ነው
መጋቢት 5 2018 ዓ.ም
አዳማ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
" የከፍተኛ አመራር ዓርኣያነት፤ ለፀረ ሙሥና ትግል ያለው ፋይዳ " በሚል መሪ ሃሣብ ዛሬ ለፕላንና ልማት ዘርፍ ከፍተኛ አመራሮች የሥራ ላይ ስልጠና እየተሠጠ ነው።
እየተካሔደ የሚገኘው ሥልጠና ዋነኛ ዓላማ ከፍተኛ አመራሮች በሥራ ወቅት የሚገጥማቸውን ጥቅም ነክ ግጭቶች ቀድሞ ለመከላከል እንዲሁም ችግሩ ከተከሰተ ሥነምግባራዊ ሙያን የተላበሰ ውሳኔ እንዲሰጡ የሚያሥችል ወጥ ሥርዓት ለማስፈን ያለመ መሆኑን የፕላን እና ልማት ሚኒሥቴር ሚኒሥትር ዲኤታ ወ/ሮ ጥሩማር አባተ በሥልጠናው ማስጀመሪያ ወቅት ተናግረዋል።
ኃላፊዋ አክለውም ሥነ-ምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥ በተቋማት ውስጥ የታማኝነት፣ የተጠያቂነት እና የግልፀኝነት ባሕል እንዲጠናከር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እደሚኖረው ተናግረዋል።
የፌዴራል የሥነ-ምግባር እና ፀረ-ሙሥና ኮሚሽን ወትሮ ሙሥናን ለመከላከል በሁሉም ተቋማት ተመሣሣይ ሥልት ይከተል እንደነበር የጠቀሡት የፌዴራል የሥነ-ምግባር እና ፀረ-ሙሥና ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር አቶ ፍቃዱ ሠቦቃ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይህ አሰራር መቀየሩን ተናግረዋል።
እንደ ም/ኮሚሽነሩ ገለፃ የፀረ-ሙሥና ትግሉ አሰራር የተቋማትን የተናጥል ባሕሪይ ከግምት ያስገባና ዘርፍ ተኮር ሆኗል ብለዋል።
በዚህም አሰራር ተቋማትን በተጨባጭ ባህሪያቸው ማለትም ፍርድ ቤቶች፣ ህዝባዊ ተቋማት፣ የልማት ተቋማት ወዘተ ብሎ በመለየት ተጨባጭ ባህሪያቸው ከግምት ያስገባ የፀረ-ሙሥና መከላከል ሥራ እንደሚተገበር ኮሚሽነር ፍቃዱ ገልፀዋል።
የዕለቱ ሥልጠና ከፍተኛ አመራሮች ለፀረ-ሙሥና ትግል ያላቸው ሚና፣ የጥቅም ግጭቶችን ቀድሞ መለየት የሚቻልባቸው ሥልቶች፣ የሥነ-ምግባራዊ ውሳኔ ሀገራዊ ልማትን ለማረጋገጥ ያላቸው ሚና እና ሌሎች ተያያዥ ሃሳቦችን በመዳሰሥ እንደሚቀጥል ታውቋል።