Previous Next

በመንግስት እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎች ለአካባቢ ጥበቃ ስራ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ተገለጸ ።

በመንግስት እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎች ለአካባቢ ጥበቃ ስራ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ተገለጸ ።
ሐምሌ 11/2017 ዓ.ም
አዳማ
፡፡፡፡፡፡፡፡።፡።፡፡፡፡።፡፡፡።።@፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡።።።
ሀገር አቀፍ የአካባቢ ህግ ቁጥጥር እየተገመገመ ነው ። የግምገማ መድረኩን በንግግር የከፈቱት የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፍሬነሽ መኩሪያ በመንግስት እየተሰሩ ያሉ የኮሪደር ፣ የአረንጓዴ አሻራ ፣ ጽዱ ኢትዮጵያ እና የወንዝ ዳሪቻ የልማት ስራዎች ለአካባቢ ጥበቃ ስራ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ገልፀዋል ። በተለይ መንግት ትክረት ተሰጥተው እየተሰሩ ያሉ የከተሞች የልማት ስራዎች ምቹ የኑሮ አካባቢ እየተፈጠሩ መሆኑን ተናግረዋል። የአካባቢ ቁጥጥር ከሀገራዊ የልማት አጀንዳ ጋር የተቀናጀ በመሆኑ የተፈጠሩትን መልካም ሁኔታዎችን በመጠቀም የአካባቢ ህግ ቁጥጥር ስራዎች በተጠናከረ ሁኔታ እየተተገበረ መሆኑን ገልጸዋል ።
ሀገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ ያለውን ፅዱ ኢትዮጵያ ባህል ማድረግ የህዝብ ንቅናቄ ግንዛቤን የመፍጠር ፣ የአካባቢ ህግን የማስከበር ፣ የተሻሻለ አፈጻጻም ያላቸው ግለሰቦች እና ተቋማት እውቅና የመስጠት እና የአረንጓዴ አሻራ ስራዎች በትኩረት እንደምሰራ ክብርት ወ/ሮ ፍሬኔሽ ተናግረዋል ።
በ2017 ዓ.ም ሰፊ የግንዛቤ ሥራ በመሰራቱ የተወሰኑ የጥራት ችግሮች ቢኖሩም የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ከፍተኛ ትህምርት ተቋማት ፣የአምራች እንዱስትሪዎች ፣ የከተሞች የቆሻሻ አያየዝ እና አወጋገድ ስርዓት እየተሻሻለ መምጣቱን ሪፖርት ቀርቧል።##
በመድረኩ ላይ የሁሉም ክልሎች እና የሁለቱ ከተማ መስተዳደሮች የአካባቢ ጥበቃ ኃላፊዎች እና ባለሞያዎች ተገኝተዋል ።
የግምገማ መድረኩ ማጠቀለያ ላይ የ2018 ዓ.ም የትኩረት አቅጣጫ ላይ ውይይት ይካሄዳል ተብለው ይጠበቃል ።
ፅዱ ኢትዮጵያ ባህል እናደርጋለን !!
====================================
የኢፌዲሪ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን
ቀጣዮችን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ
ድረገጽ https://epa.gov.et/
ኤክስ (ትዊተር) https://twitter.com/epaethiopia

የባለስልጣንኑ አድራሻ

አድራሻ፡ አራት ኪሎ ከአብርሆት ቤተመጻሕፍት በስተጀራባ ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አጠገብ፣ አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 9

ስልክ፡ +251 (0)11-170-4038/4150

ፋክስ፡ +251 (0)11-170-4158/ 45

ኢመይል   Info@epa.gov.et

ቲውተር  https://twitter.com/epaethiopia

ፌስቡክ   https://www.facebook.com/MefEth/

ቴሌግራም   https://t.me/efcccethiopia

ፖ.ሳ.ቁ      12760

አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ