ሁለተኛው ዙር ጽዱ ኢትዮጵያን ባህል ማድረግ ክልል አቀፍ ንቅናቄ መድረክ ክቡር ሐጂ አወል አርባ የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት በተገኙበት በሰመራ ከተማ በዛሬው ቀን በይፋ ተጀመረ።
================
ክቡር ሐጂ አወል አርባ የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ክልል አቀፍ መድረኩን በይፋ በንግግር ያስጀመሩ ሲሆን፤ አካባቢን በመጠበቅና በአግባቡ በመጠቀም ዘላቂ፣ ጽዱና ጤናማ አካባቢን ለመፍጠር የፖለቲካ ቁርጣኝነት የሚጠይቅ ሲሆን በየወቅቱ የአካባቢ አጠቃቀማችን ኦዲት መድረግ ይገባል።ማንኛውም የልማት ሥራ አካበቢን በማይበክልና የአካባቢ ዘላቂነት ባረጋገጠ መልኩ መሆን እንዳለበት በማንሳት የህግ ተከባሪነት ሥራዎችም በተቀናጀ መልኩ የሚፈፀም ይሆናል ብለዋሉ።
የሀገር አቀፍ ንቅናቄ መድረኩን ተከትሎ ዛሬ በክልላችን የተጀመረው የአካባቢ ብክለት መከላከል ንቅናቄው በክልሉ ውጤታማ እንዲሆን በተቀናጀ መንገድ ተግባራዊ እንደምያደርጉም አረጋግጠዋሉ። ክብርት ኢንጂነር ለሊሴ ነሜ የኢፌዲሪ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተርን የክልሉ የአካባቢ አበምባሰደር አድርገው በመሰማቸውንም ገልፀዋሉ።
ክብርት ኢንጂነር ለሊሴ ነሜ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር በክልሉ የንቅናቄ መክፈቻ መድረክ ላይ ባስተላለፉት መልዕክታቸው አካባቢን የመጠበቅ፣ የመንከባከብና ጽዱና ንፁህ አካባቢ በማድረግ ለኑሮ ምቹ መድረግ የሁሉ ህዝብ ኃላፊነትና ግዳታም አባክረው መልዕክት አስተላልፈዋሉ።
በክልሉ እስካሁን ድረስ ለተሰራው ሥራዎች በማመስገን ክልል አቀፍ ንቅናቄውም ውጤታማ እንዲሆን በቅንጅት መሰራት ወሳኝ መሆኑን በማንሳት ሁሉም የአካባቢ ብክለትን በመከላከል የአካባቢ አምባሰደር መሆን ይጠበቃል ብለዋሉ።
የክልል አቀፍ ንቅናቄ መድረኩም የክልሉ ፕሬዝዳንት እና ከፍተኛ የክልሉ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በጽዳት ዘመቻ፣ በአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከለ፣ እና ጽዱ ኢትዮጵያን ባህል ማድረግ በሚል ቃል ሰነጀድ ቀርቦ የፓናል ውይይት በማካሃድ ሁለተኛ ዙር ክልል አቀፍ ንቅናቄ በፓሊስ ማርሽ ታጀቦ በድምቀት ተጀምሯል።
====================================
የኢፌዲሪ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን
ቀጣዮችን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ