ሁለተኛዉ ዙር ሀገርአቀፍ የብክለት ቅነሳ ንቅኔቄ በይፋ ተጀመረ።
ግንቦት 2017ዓ.ም
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡።።፡፡፡@።።።።።።።።።።።
ሁለተኛውን ሀገር አቀፍ የብክለት ቅነሳ ንቅናቄን ከፍተኛ አመራሮች፣አምባሳደሮች፣ ባለድርሻ አካላት እና በዘርፉ ላይ የሚሰሩ ግብረሰናይ ድርጅቶች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተጀምሯል።
የዕለቱ የክብር እንግዳ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አደም ፋራህ ንቅናቄውን ባሰጀመሩበት ወቅት እንደገለፁት ፅዱ ኢትዮጵያ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ሀሳብ አመንጪነት እና አመራር ሰጪነት ወደ ተግባር በመቀየር ባለፉት ሰባት አመታት
በስድስት አበይት ጉዳዮች ማለትም በአረንጓዴ አሻራ፣ የከተማ ኮሪደር ልማት፣የገጠር ኮሪደር ልማት፣የታዳሽ ኃይል አጠቃቀምን ማስፋፋት፣ዘመናዊ የቆሻሻ አያያዝ ዘዴዎች ማስፋት እንዲሁም የህግና የተቋም ስራዎችን ማሻሻል ረገድ አመርቂ ውጤቶች
ማስመዝገብ መቻላቸውን ጠቅሰው በቀጣይ ለንቅናቄው መሳካት ከመላው ህዝባችን ጋር በቅንጅት መስራት ይጠበቃል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የአዲስ አበባ ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አበቤ በበኩላቸው መዲናችንን ፅዱና ለኑሮ ምቹ ከማድረግ የሚታይ ለውጥ በማምጣት በአረንጓዴ አሻራ በመዲናዋ ከነበረው 2.8% የደን ሽፋን ወደ 20% ማደጉን ፣ከ76 በላይ ወንዞችና ጅረቶችን የማከም ስራ እየተሰራ መሆኑን ፣241ኪ.ሜ የሳይክል መንገድ መሰራቱን እንዲሁም በኤሌትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ወደ ስራ ማስገባት መቻሉን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ አካባቢ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክብርት ኢንጅነር ለሊሴ ነሜ የአካባቢ ጥበቃ ስራ የቅንጦት ስራ ሳይሆን የአካባቢ መብት ወይም ምቹ የኑሮ አካባቢ የመኖር መብት ነው ብለዋል። የአካቢን የመጠበቅ የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት መሆኑን በመጥቀስ ለንቅናቄው መሰካት ሁሉንም የበኩሉን ኃላፊነት እንዲወጣ ጠይቀዋል ።