ፅዱ ኢትዮጵያን ባህል ማድረግ እና ዘላቂ ልማት ለማረጋገጥ የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ እንደሚያስፈልግ ተገለጸ ።
ግንቦት 28/2017 ዓ.ም
"""""'''''''''''''''''''''''"""""'@""""""'""''"""""""
የሁለተኛው ዙር ፅዱ ኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄ የማስጀመሪያ ስነ ስርዓት አካል የሆነ የግሉ ዘርፍ ሚና በሚል የተዘጋውን የፓናል ውይይት በንግግር የከፈቱት የኢንዱስትሪ ሚንስቴር ሚንስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሀሰን ሙሐመድ ፅዱ ኢትዮጵያን ባህል ማድረግ እና ዘላቂ ልማት ለማረጋገጥ የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ ወሳኝ ሚና እንዳለው ገለጹ ።
የህዝብ ቁጥር በመጨመሩ ምክንያት የሰው ልጅ ፍላጎትን ለማሟላት ኢንዱስትሪዎች በመስፋፋታቸው የቆሻሻ ዓይነትና መጠን መጨመሩን ክቡር አቶ ሀሰን አብራርተው በውሃ ፣ በአየር እና በአፈር ብክለትና በአጠቃላይ በተፈጥሮ ሀብት ላይ ጉዳት እያደሰ መሆኑን አንስተዋል። በመሆኑም የተፈጥሮ ሀብቶቻችን ከብክለት ለመጠበቅ የግል ድርጅቶች ቆሻሽን በመቀነስ ፣ መልሰው ጥቅም ላይ በማዋል እና አካባቢያዊ ተቀባይነት በለው ዘዴ ምርት እንዲያመርቱ ጠይቀዋል ።
የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ምክልት ዋና የዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፍሬነሽ መኩሪያ የሁለተኛ ዙር የብክለት ቅነሳ የህብረተሰቡን ግንዛቤ የማሳደግ ፣አረንጓዴ አሻራን አጠናክረው ማስቀጠልና የአካባቢ ህጎችን የማስከበር ላይ ትክረት በመስጠት እንደምሰራ ገልጸዋል። በመሆኑም የፅዱ ኢትዮጵያ ዓላማን ለማሳካት ጉዳዩ የሚመለከታቸው በተለይ ከግሉ ዘርፍ በንቀት መሳተፍ እንዳለባቸው ጠይቀዋል ።
የግል ድርጅቶች በተለይ የፕላስቲክ፣ ኬሚካልን እና የተቃጠለ የሞተር ዘይት መልው ጥቅም ላይ የሚያውሉ ፣ ቀልዝን የሚያመርቱ ድርጅቶች ተሞክሮአቸውን ለሌሎች ያካፈሉ ሲሆን በስራቸው ውጤታማ መሆናቸውን ፣ለብዙ ዜጎች የስራ መፍጠራቸውን ፣ አካባቢን በመጠበቅ ማህበራዊ እና ሀገራዊ የኃላፊነታቸውን እየተወጡ መሆናቸውን ገልጸዋል ።
በፓናል ውይይቱ ላይ ከወጣት ማህበራት፣ የግሉ ዘርፍ የትምህርት ተቋሟት ተኃላፊዎችና ባለሙያዎች ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል ።
====================================
የኢፌዲሪ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን
ቀጣዮችን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ