"ፅዱ ኢትዮጵያ ባህል ማድረግ" ሀገራዊ ንቅናቄ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ንቅናቄ አካል የሆነ የማስጀመሪያ ፕሮግራም ዛሬ ሰኔ 18/2017 ዓ. ም ማለዳ 12:30 ጀምሮ በጀግናው ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ ስም በተሰየመው አደባባይ መነሻ በማድረግ በክቡር ከንቲባ አቶ ዳዊት ጡምደዶ የሆሳዕና ከተማ ከንቲባ፣ የማዕከላዎ ኢትዮጵያ የደን አካባቢ ጥበቃ እና ልማት ቢሮ ሀላፊ ክቡር አቶ አብርሀም መጫ እንዲሁም የፌደራል አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢ/ን ለሊሴ ነሜ በተገኙበት የከተማ ፅዳት፣ የከተማ ኮሪደር ልማት ጉብኝት እና የአረንጓዴ አሻራ አካል ችግኝ ተከላን ሀዲዪ ነፈራ ሜዳ ፓርክ ፕሮግራሙ ተጀምሯል። በዚህ የዘመቻ ስራ ላይ የከተማ መስተዳድር አመራሮች፣ የክፍለ ከተሞችና የቀበሌ አመራሮች፣ የከተማ ነዋሪዎች እና የፌደራል አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አመራሮች ታዳሚ ሆነዋል።






