የፕላን ልማት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት 22ኛው ዓለምአቀፍ የፀረ ሙስና ቀን በጋራ አከበሩ።
ህዳር 24/2018ዓ.ም
በዓሉ በአለምአቀፍ ደረጃ ለ22ኛ ጊዜ ''ትውልድን በስነምግባር፤ተቋምን በአሰራር'' በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል። በበዓሉ አከባበር ላይ መልዕክት ያሰተላለፉት የፕላን ልማት ሚኒስቴር ሚኒስቴር ዲኤታ ክብርት ወ/ሮ ጥሩማር አባተ እንደገለፁት ኢትዮጵያ የአለምአቀፍ የፀረ ሙስና ኮንፌንሽን አባል ሀገር እንደመሆኗ መጠን በዓሉን ላለፉት 21አመታት እየተከበረ መምጣቱን በመግለፅ መንግስት ትውልድን በስነ ምግባር ከመገንባት ባሻገር ዘመናዊ አሠራር ስርዓቶችን በመዘርጋት ዜጎችን ማገልገል ላይ ትኩረት በመስጠት እየተሰራበት መሆኑን ጠቁመዋል። ምኒስቴር ዲኤታዋ በገለፃቸው ህግ፣ደንብና አሠራርን ጠብቆ መስራት ላይ ተቋማት ትኩረት ሰጥተው መስራት እንዳለባቸው በመግለፅ ሙስናን ለመዋጋት ሁሉም የበኩሉን አስተዋፅኦ ማበርከት እንዳለበት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የፌዴራል ስነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ክቡር አቶ እሸቴ አስፋው በበኩላቸው የፀረ ሙስና ትግል ባለቤት ተቋማትና አመራሩ መሆኑን በመግለፅ ትውልድን በስነምግባር መገንባት እንዲሁም ተቋማትን በአሰራር ስርዓት ማዘመን በተለይም በአገልግሎት አሰጣጥ እና በመንግስት ግዥ ላይ እንዲሁም እያንዳንዱ ፕሮጀክቶች የአካባቢ ጥበቃን ጉዳይ ያማከሉ እንዲሆኑ አስቻይ ሁኔታዎችን መፍጠር ላይ በትኩረት መሰራት እንዳለበት አሳስበዋል።
በበዓሉ አከባበር ላይ የፕላን ልማት ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት አመራሮች ለፌደራል ስነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የሀብት ምዝገባ ርክክብ አካሂደዋል።