የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባስልጣን ሀገራዊ የሙቀት አማቂ ጋዞች ልቀት ቅነሳ ፣ ዘገባና ማረጋገጫ ስርዓትን በጋራ ለመስረት ከሰባት ፌዴራል ዘርፍ መ/ቤቶች ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ ።
ለታህሳስ 16/2017 ዓም
አዲስ አበባ
*@***
የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባስልጣን ሀገራዊ የሙቀት አማቂ ጋዞች ልቀት ቅነሳ ፣ ዘገባና ማረጋገጫ ስርዓትን በጋራ ለመስረት ከሰባት ፌዴራል ዘርፍ መ/ቤቶች ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ ።
በመግባቢያ ስምምነት ስነስርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክብርት ኢንጂነር ሌሊሴ ነሜ
ባለስልጣን መ/ቤቱ በህግ የተሰጠውን ስልጣንና ተግባር በብቃትና በኃላፊነት ለመወጣት እና ሀገራዊ የሙቀት አማቂ ጋዞች ልቀት ቅነሳ ፣ዘገበ እና ማረጋገጫ ስራዎች ለመጠናከር ወደ ስራ በመግባት የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ በመግለጽ፣ፖሊሲዎችና አዋጆችን፣ ደንቦችና ስትራቴጂዎችን በመተግበር ፣የአካባቢ ጉዳቶችን ለማስቀረት በጋራ ለመስረት ከመቼውም ጊዜ በላይ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትን በመሳተፍ እየሰራ መሆኑን ገልጿል።
ሀገራችን በ2030 የሙቀት አማቂ ጋዞች ልቀትን በ68.8% ለመቀነስ ቃል የተገባውን ለማሳከት በቅንጅት መስረት እና ሁሉም ኃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት ጠይቀዋል።
በፊርማ ስነስርዓቱ ላይ የተገኙት የሰባቱም ዘርፍ መ/ቤቶች ኃላፊዎች በጋራ ለመሰራት ቃል ገብተዋል ።
በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 545/2016 ለኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ከተሰጡት የተለያዩ ስልጣንና ተግባር መካካል አንዱ የሙቀት አማቂ ጋዞች ልኬት ስራዎችን በማካሄድ የማረጋገጥ ፣ በሌሎች የተደረጉ የሙቀት አማቂ ጋዞች ልኬቶችን የማረጋገጥ የመቆጣጠር እንዲሁም ለሚመለከተው አካል ሪፖርት የማቅረብ ኃላፊነት አንዱ ነው።
==================================
የኢፌዲሪ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን
ቀጣዮችን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ