የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ጋር በተለያዩ መስኮች በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ።
መስከረም 27/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ
የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክብርት ኢንጅነር ለሊሴ ነሜ ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የማኔጅመንት አባለት ጋር በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን በመገኘት እየተሰሩ የሚገኘውን የተለያዩ ሥራዎችን ጉብኝት አካሂደዋል።
በጉብኝቱ ወቅት የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጅነር ዮናስ አያሌው ኮርፖሬሽኑን ባስጎበኙበት ወቅት ኮርፖሬሽኑ የኮንስትራክሽን ተግባራትን ዘመናዊና ዲጅታል በሆነ መንገድ በመከታተልና ችግር ፈቺ ተግባራትን ማከናወኑንና በተለያዩ ወርክሾፖች የመልሶ መጠቀም ፣ የእንጨትና የብረት ስራዎች እንዲሁም የአልሙኒየም እና በኮርፖሬሽኑ የሚሰሩ ሌሎች ስራዎች ተጎብኝተዋል።
ክብርት ኢንጅነር ለሊሴ ነሜ በጉብኝቱ ወቅት ኮርፖሬሽኑ በአጭር ጊዜ ውስጥ ስር ነቀል ለውጥ በማስገንዘብ ምሳሌ የሚሆኑ በሀገር ውስጥ ከውጭ የሚገቡ የተለያዩ ምርቶችን የሚተካ መሆኑንና በተለይም የአካባቢ ጥበቃን ስራ ከማገዝ አንፃር ኡደታዊ ስነ ምጣኔ (ሰርኩላር ኢኮኖሚን) መልሶ መጠቀምን በተግባር ማሳየቱን ለዚህም የአረንጓዴ ሰርተፊኬት የሚገባው መሆኑን በመግለፅ ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጋር በተለያዩ መስኮችን በትብብር በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ላይ መደረሱን ገልፀዋል።
አብሮ ለመስራት የሚያስችለውን የስራ ስምምነት የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጅነር ዮናስ አያሌው እና የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ኢንጅነር ለሊሴ ነሜ ተፈራርመዋል።
====================================
የኢፌዲሪ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን
ቀጣዮችን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ