የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን እና ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን (ፋና) ፅዱ ኢትዮጵያን ለትውልድ ለማሻገር በጋራ ለመስራት የሚያስችል ውይይት አካሄዱ።
ሚያዝያ 08/2017ዓ.ም
@
ውይይቱ የተካሄደው የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ከፍተኛ አመራሮች በፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን (ፋና)ጉብኝት ባካሄዱበት ወቅት ነው።
የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክብርት ኢኒጅነር ለሊሴ ነሜ በጉብኝቱ ወቅት እንደገለፁት የአካባቢ ጥበቃ ስራ የሁሉንም ተሳትፎ የሚፈልግ በተለይም የሚዲያ ድርሻ ደግሞ ጉልህ መሆኑን በመጥቀስ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ሀሳብ አመንጪነት ፅዱ ኢትዮጵያን ለትውልድ ለማስተላለፍ በሚደረገው የብልጽግና ጉዞ የአረንጓዴ አሻራ፣ የኮሪደር ልማት እንዲሁም የወንዝ ዳርቻ ልማት ስራዎች በትኩረት እየተሰሩ መሆናቸውን ገልፀው በቀጣይ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የማህበረሰቡን ግንዛቤ ከማሳደግ በተጨማሪ የአካባቢ ጥበቃ ህጎች ማስከበር ላይ በትኩረት ለመስራት የሚያስችል ሀገር አቀፍ የፅዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ እንደሚጀመርና ለንቅናቄው መሳካትም ሚዲያዎች ጉልህ ተሳትፎ እንደሚጠበቅ አስታውቀዋል።፡
ኢኒጅነር ለሊሴ አክለውም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ለሚያስጀምረው እና ለስድስት ወራት በሚቆየዉ ''ፅዱ ኢትዮጵያ '' ሀገር አቀፍ ንቅናቄ የማህበረሰብን ግንዛቤ ለማሳደግ እና የአካባቢ ህግ ተከባሪነት ለማረጋገጥ እንደሚረዳ ጠቁመዋል።
የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አድማሱ ዳምጠው በበኩላቸው ከአካባቢ ጥበቃ ጋር መስራት ለነገ የተሻለ ሀገር ለመፍጠር በሚደረገው የብልፅግና ሂደት ፋና የራሱን አሻራ የሚያሳርፍበት እና አካባቢዋ የተጠበቀ ኢትዮጵያን ለማብሰር በጋራ የመስራት ኃላፊነት እንዳለበት በመግለፅ ተባብሮ በመስራት ሀገራዊ ኃላፊነታቸው ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል ።
====================================