የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን እና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) ፅዱ ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በትብብር ለመስራት ተስማሙ።
የመጋቢት 09/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ
=================================================================
የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ የባለስልጣን ከፍተኛ አመራሮች በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) ጉብኝት ባካሄዱበት ወቅት በትብብር ለመስራት ተስማሙ።
የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክብርት ኢኒጅነር ለሊሴ ነሜ በጉብኝቱ ወቅት እንደገለፁት መንግስት በሀገር ሚዲያ ላይ ትኩረት በመስጠት በተለይም አካባቢን ዘላቂነት ከመጠበቅና ስነ ምህዳርን ከማስጠበቅ ፣ በቴክኖሎጂ፣ ሰው ተኮር እና ፅዱና ንፁህ አየር ያለበት በመሆኑ ኢቢሲ ለሌሎችም ተቋማት ምሳሌ መሆኑን ገልፀዋል።
ባለስልጣኑ ከኢቢሲ ጋር ከዚህ ቀደም አካባቢ ጥበቃን በተመለከቱና የህብረተሰቡን ግንዛቤ የሚጨምሩ ሰፊ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን በመግለፅ በቀጣይም ይህንኑ አጠናክሮ በትብብር ለመስራት እንደሚፈልጉ ገልፀዋል።
ክብርት ኢኒጅነር ለሊሴ አክለውም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በቀጣይ ወር ለሚያስጀምረው እና ለስድስት ወራት በሚቆየዉ ''ፅዱ ኢትዮጵያ '' ሀገር አቀፍ ንቅናቄ የማህበረሰብን ግንዛቤ ለማሳደግ እና የአካባቢ ህግ ተከባሪነት ለማረጋገጥ የሚዲያ ድርሻ ወሳኝ መሆኑ ከኢቢሲ ጋር በልዩ ሁኔታ ለመስረት እንደሚፈልጉ ገልጸዋል ።
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን(ኢቢሲ) ዋና ስራ አስፈፃሚ ክቡር አቶ ጌትነት ታደሰ በበኩላቸው ኢቢሲ የአካባቢ ጥበቃ ጉዳይን ለማህበረሰቡ ዘንድ ግንዛቤ ለማሳደግ በቀጣይነት በቅንጅት እንደሚሰሩ በተለይም በልጆች ፕሮግራሞች ላይ የአካባቢ ጉዳይ ትኩረት በማድረግ ቢሰራ ውጤት እንደሚመጣ በመጠቆም ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር ተባብሮ በመስራት ሀገራዊ ኃላፊነታቸው ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል ።
====================================



