የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ለአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች የአረንጓዴ ቴክኖሎጂ የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡
ግንቦት 4/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ
====================
የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ትምህርት ቤቶቻቸውን አረንጓዴና ፅዱ በማድረግ የተሻለ ሥራ ለሰሩ ለሁለት አዲስ አበባ ከተማ ት/ቤቶች በፀሐይ ኃይል የሚሰራውን ታዳሽ ሶላር ማብራቶችንና የስፖርት ቁሳቁሶችን በትምህርታቸው ውጤታማ ለሆኑ ለ290 በየካ ለደጅ አዝማች ወንድረድ እና በለሚኩራ ለድል ጮራ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ድጋፍ ተደረገ፡፡
ክብርት ዶ/ር ለሊሴ ነሜ የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር በድጋፍ አሰጣጥ መርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት በትምህር ቤቶቹ ግቢ ፅዱና አረንጓዴ መሆኑ በሀገር አቀፍ ደረጃ ሞዴል መሆኑን በመንሳት ለትምህርት ቤቱ አመራሮችና ማህበረሰቡ ከፍተኛ ምስጋናቸውን በማቅረብ፤ ከተለያዩ ሀገራት ድጋፍ በመፈላለግ የተገኘውን በፀሐይ ኃይል የሚሰሩ የግሪን ቴክኖሎጂ ሶላር መብራቶች ዕቀዎችን በትምህርት ቤቶች ለደረጃ ተማሪዎች እና የተለያዩ የስፖርት ቁሳቁሶችን ለት/ቤቱ አስረክበዋሉ፡፡ ፅዱ፣ጤናማና ለመኖሪያ ምቹ የሆነውን አረንጓዴ አካባቢ በመፍጠር ለትውልድ ማስተላለፍ የዛሬው ትውልድ ኃለፊነት በመሆኑ ሁሉም የህብረሰብ ክፍሎችን አካባቢው በማፅዳትና አረንጓዴ በማድረግ የዜግነት ግዴታውን እንዲወጡ አሳስበዋሉ፡፡
ክብርት ዶ/ር ለሊሴ አክለውም በትምህርት ቤቱ በአካባቢ ክበብ በመደራጀት ፅዱ የመመሪያ ክፍሎች፣ ፅዱ የትምህርት ቤቱ ግቢና አራንጓዴ አካባቢ እንዲሆን አስተዋፅኦ ላበረከቱ ተማሪዎች የአካባቢ ክባብ ተማሪዎችን በማመስገን ድጋፍና ማበረታቻ በቀጣይነት እንደሚደረግላቸውም አስሳባዋሉ፡፡

