የኢ.ፌ.ዲ.ሪ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን አመራሮችና ሠራተኞችን የአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ አካሄደ፡፡
ሐምሌ 24 2017 ዓ ም
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን አመራሮች እና ሠራተኞች ከኦሮሚያ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን፣ ከሸገር ከተማ አስተዳደር ገለና ክፍለ ከተማ ጋር በመቀናጀት በኦሮሚያ ክልል በገላን ክፍለ ከተማ በአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ ዘመቻን በስኬት ተካሄደ፡፡
በብሔራዊ ደረጃ በአንድ ጀምበር ሰባት መቶ ሚሊዮን የችግኝ ተከላ ለማካሔድ በመንግስት ደረጃ በታቀደ መሠረት ሁሉም የባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ሠራተኞችና አመራሮች በተቀናጀ መል በዛሬው ዕለት ከ4500 የተለያዩ ዝርያ ችግኞችን በሸገር ከተማ የገላን ክፍለ ከተማ ኮረብታ ላይ የችግኝ ተከላ አካህዷል።
የዕለቱን የተከላ መርሃ-ግብር መልዕክት በማስተላለፍ ያስጀመሩት የአካባቢሚ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ክብርት ኢንጂነር ለሊሴ ነሜ እና የኦርሚያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሠይፈዲን መሀዲ ሲሆኑ፤ ባስተላለፉት በመልዕክታቸው ዛሬ የተካሄደው የችግኝ ተከላ ቋሚ እንክብካቤ እና ጥበቃ ስለሚያስፈልገው ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ አሳስበዋል።
የተቋሙ የበላይ አመራሮች ከመላ ሰራተኛው ጋር በመሆን ተከላ ያካሔዱ ሲሆን በቀጣይ የተተከሉ ችግኞችን የመጠበቅ የማረም እና በበጋው ወራት ተከታትሎ ውሃ የማጠጣት ቋሚ ስራ እንደሚኖር ተገልጿል።
በተከላው የተሳተፉ ሰራተኞች በበኩላቸው በአንድ ጀምበር ሠባት መቶ ሚሊዮን የችግኝ ተከላ ዘመቻን ተሳትፈው በስኬት መጨረሳቸው ለቀጣይ መሰል የልማት ስራ የመነሻ ስንቅ እደሚሆናቸው ተናግረዋል።
በጠንካራ መሰረት ላይ የፀናች ሀገር ለመገንባት የአካባቢ ሀብትን በዘላቂነት ማልማት ወሳኝ መሆኑን በማመን የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ ሥራ በዓይነት፣ በመጠን እና በስልት እየተጠናከረ ከመጣ ዘንድሮ ሰባተኛ ዓመቱን የያዘ ሲሆን ተጠናክሮ ባህል ሆኖ መቀጠል እንደለበት አስተያታቸውን ሰጥተዋሉ።
====================================
የኢፌዲሪ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን
ቀጣዮችን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ