የኢ.ፌ.ዲ.ሪ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን በቅርቡ በፀደቀው የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ አዋጅ ዙሪያ የተቀናጀ አተገባበር እንዲኖር ለማስቻል ያለመ ምክክር ከባለድርሻ አካላት ጋር አካሔደ
መሥከረም 15 2018 ዓም
አዲስ አበባ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ ሥርዐትን ለማዘመን በፀደቀው አዋጅ 1383/2017 ዙሪያ ከጎማ እና ከፕላስቲክ ከረጢት አምራቾች ጋር ምክክር አደረገ።
በቅርቡ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መንግሥት የሀገርን ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ ለውጥ ዕውን ለማድረግ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሥርዓትን እየተገበረ ይገኛል ።
የዚሁ የማሻሻያ ሥርዓት ማዕቀፍ አንደኛው ክፍል የሆነው የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታን ለመተግበር ደግሞ አንዱ መሠረት የተቀናጀ የአካባቢ ጥበቃ እና ልማትን በማሥፈን የፅዱ ኢትዮጵያን ዕሳቤ ማሳካት ነው።
ይህንን የፅዱ ኢትዮጵያን ዕሳቤ በማሳካት የራሱን ሚና እንደሚወጣ የታመነበት የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ አዋጅ ዝርዝር የአተገባበር ሒደቶችን አስመልክቶ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር አድርጓል ።
የአዋጁን አተገባበር የተቀናጀ ለማድረግ ዛሬ የተዘጋጀውን መድረክ መልዕክት በማሥተላለፍ ያሥጀመሩት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሪክተር ክብርት ኢንጂነር ለልሤ ነሜ ሲሆኑ የአዋጁን ጠቀሜታ አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት:-
- የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድን ማዘመን በብክለት ሳቢያ በሰው፣ በእንሥሳት እና በአካባቢ ላይ የሚደርሰውን ዓይነተ ብዙ ጠንቆች አስቀድሞ መከላከል ማቻሉን፤
- የማይበሰብሱ እና ለአንድ ጊዜ ብቻ አገልግሎት የሚሰጡ የፕላስቲክ ከረጢቶች እያደረሱት ያለውን ሁለንተናዊ ቀውሥ መግታት ማስቻሉን፤
- የተራዘመ የአምራቾች ኃላፊነትን እንዲሰፍን ማስቻሉን፤
- የኡደታዊ ኢኮኖሚን (መልሶ መጠቀምን) ማበረታታቱን ወዘተ መሆኑን በዓፅንኦት ገልፀዋል።
- በተቋሙ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ ዴሥክ ኃላፊ አቶ ዋሲሁን ዓለሙ በበኩላቸው ለአዲሡ አዋጅ መፅደቅ ዋነኛ ምክኒያት የሆኑ ጉዳዮችን በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን የአዋጁ ቀጣይ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታውንም አብራርተዋል።
የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ ሥርዓትን በማዘመን የፅዱ ኢትዮጵያን ዕሳቤ ለማሳካት ጉልህ ሚና ዕንደሚኖረው በታመነበት አዋጅ አተገባበር ዙሪያ በተካሔደው የውይይት መድረክ የጎማ እና ፕላሥቲክ አምራች ማህበር ተወካዮች እና አምራቾች የተለያዩ ጥያቄዎች አቅርበው የተቋሙ የበላይ ኃላፊዎች መልሥ እና ማብራሪያዎች ሰጥተዋል።
====================================
የኢፌዲሪ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን
ቀጣዮችን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ