የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ከኢትዩ-ቴሌኮም ጋር የአካባቢ ጥበቃ ጉዳይን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ደግፎ ለመስራት በከፍተኛ አመራሮች ደረጃ ውይይት አደረጉ፡፡
የካቲት 2017ዓ.ም
አዲስ አበባ
=========================================
የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ከኢትዩ-ቴሌኮም ጋር በአካባቢ ብክለት መከላከልና መቆጣጣር፣ ቆሻሻ አስተዳዳርና የማስወገድ ስርዓት፣ የአካባቢና ማህበራዊ ተፅዕኖ ግምገማ ስርዓት፣ የስርዓተ ምህዳትና ብዝሀ ህይወት አጠቃቀም ቁጥጥር፣ በአካባቢ የሙያ እና የብቃት ማረጋገጫ ስርዓት፣ የቢሮ አገልግሎትን ማዘመን እንዲሁም የአካባቢ መረጃ አስተዳደርን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ማስደገፍ የሚያስችል ውይይት አደረጉ፡፡
በሁለትዮሽ ውይይቱ ላይ ክብርት ኢንጂነር ለሊሴ ነሜ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር የኢትዩ-ቴሌኮም በሀገራችን ካሉ አንጋፋ ተቋም መሆኑን በመጥቀስ በአካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ላይ ለባለፉት ዓመታት ላደረገው ድጋፍ እንዲሁም
አሁንም ለተጠየቀው ድጋፍ ፍቃደኛ መሆን ምስጋና አቅርበዋል፡፡ በተለይም የሚከናወኑ ተግባራትን በዲጂታል ቴክኖሎጂ አስደግፎ ማስደገፍ ላይ ከኢትዩ ቴሌኮም እገዛ እንዲሚፈለግ ተብራርቷል፡፡
ኢትዩ-ቴሌኮም የመሰረተ ልማት ቺፍ ስታፍ አቶ ታሪኩ ደምሴ ካምኒው የተሰጠውን ትርፋ ድርጅት የመሆን ተልዕኮ ጎን ለጎን ማህበራዊና አካባቢ ሀላፊነትቱ የሚወጣ በተለይም በአካባቢ ጥበቃ ጉዳይ ላይ በርካታ ስራዎችን ለአብነትም በአረንጎዴ አሻራን በማጽናት፣ የካርበን ልቀት ዝቅተኛ የሆኑ ቴክኖሎጂዎች መጠቀም፣ የታዳሽ ሀይል ምንጮችን ደፈመጠቀም፣ የአየር ብክለት ልኬት ማካሄድ፣ የኤሌክትሮኒክስና ኤሌክትሪክ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ስርዓት ማዘመን የመሳሰሉ ስራዎችን እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡ በቀጣይ ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በተለዩ ጉዳዮች ላይ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸው ገልፀዋል፡፡
በዚህ መሰረት በቀጣይ ዓመታት በአካባቢ ብክለት መከላከያና መቆጣጠር፣ የአካባቢና ማህበራዊ ተፅዕኖ ግምገማ ስርዓት፣ ብዝሀ ህይወት ጥበቃ፣ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ፣ የአካባቢ ጥበቃ ጉዳይ ጉዳዮችን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ለማስደገፍ የአጭርና የረጅም ጊዜ ሰሌዳ በማዘጋጀት ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡