የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ሰራተኞች 20ኛውን የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች በዓልን በተለያዩ ስነስርዓት አከበሩ ።
ታህሳስ 01/2018 ዓ.ም
**************@****************
የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን 20ኛው የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል “ዲሞክረሲያዊ መግባባት ለሕብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ስነስርዓት በደማቅ ሁኔታ አክብረዋል፡፡
በዓሉን በንግግር ያስጀመሩት የአካባቢ ጥበቃ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፍሬነሽ መኩሪያ 20ኛው የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል የህዳሴ ግድባችን በጋራ ጥረታችን ተገንብቶ የተጠናቀቀበት በመሆኑ በዓሉን ልዩ ያደርጋል ብለዋል፡፡ ህብረብሄራዊነታችን ጥንካሬያችን በመሆኑ በጋራ ቆመን የጋራ ሀገራዊ ጥቅማችን ማስከበር እንዳለብን መልዕክት አስተላልፈዋል ፡፡ እንደ ተቋምም እተካሄዳ ያለውን ጽዱ ኢትዮጵያን በጋራ ቆመን አውን እናደርጋለን ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓልን የሚመለክት ጽኁፍ ቀርቦ ውይይት የተካሄደ ሲሆን ሠራተኞች በመንግስት እያተካሄደ የሚገኘው የሲቪል ሰርቪስ አካታችነት ሪፎርም ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች እኩል ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ትልቅ ሚና እንዳለው ገልጸዋል፡፡ በት/ቤቶች ተማሪዎች የብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል የማክበር ጥሩ ጅማሬ እና ህብረብሄራዊነት ውበት እና ጥንካሬ መሆኑን ግንዛቤ እየተገኘ ማምጣቱንም በመግለጽ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጠይቀዋል ። በየአመቱ ልጆቻችን ቀኑን ለማክበር በጉጉት ይጠብቃሉ ብለዋል ። በመጨረሻም የወላይታ የዘመን መለወጫ በዓል "ጊፋታ" በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) በዓለም ቅርስነት በመመዝገቡም ተከትሎ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ሰራተኞች ደስታቸውን ገልጸዋል።