የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን የአካባቢ ጉዳዮች የሚሰተናገዱበት የአካባቢ ፍርድ ቤቶች በሚቋቋሙበት ሁኔታ ላይ ከበጎ ፈቃደኛ የህግ ባለሙያዎች ጋር ውይይት አካሄደ፡፡
ጥር /2018
አዲስ አበባ
================
የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ከተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት አንዱ ከሚመለከታቸው ጋር በመመካከር የአካባቢ ጉዳዮች የሚሰተናገዱበት የአካባቢ ፍርድ ቤቶች ማቋቋም ሲሆን ይህን ወደ ስራ ለማስገባት ከሰባት አመት በፊት የተለያዩ ዝግጅቶችን ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡ የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ዶ/ር ለሊሴ ነሜ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ከዚህ ቀደም ሲያከናወናቸው የነበሩ ጅምር ስራዎችን መነሻ በማድረግ፤ ከሲቪል ሶሳይት በጎ የህግ ባለሙያዎች ጋር በመሆን የሌሎች ሀገራትን ተሞክሮ በመዳሰስ፤ ከዚህ ቀደም የተዘጋጀውን ረቂቅ የህግ ማእቀፍ የመጨረሻ ቅርፅ በማስያዝ እና ተጨማሪ የባለድርሻ አካላት ውይይት በማካሄድ ረቂቅ ህጉን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለሚመለከተው አካል ለማፀደቅ ከስምምነት ላይ መደረሱን በውይይት ወቅት ማብራሪያ ሰጥተዋሉ፡፡