የሥርዓተ ምህዳር አገልግሎት ክፍያን በተጠናከረ መልኩ ተግባራዊ ለማድረግ የባለድርሻ አካላት ቅንጅት እንደሚያስፈልግ ተጠየቀ።
መጋቢት 12/2018ዓ.ም
የሥርዓተ ምህዳር አገልግሎት ክፍያ በአዋጅ ቁጥር1401/2018 የፀደቀ ሲሆን አዋጁን ተፈፃሚ ለማድረግ በቅንጅት መሰራት እንዳለበት ተገልጿል። የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ም/ዳይሬክተር ክቡር አቶ ንጉሱ ለማ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ከፋርም አፍሪካ እና አጋሮቹ ባዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለፁት ባለስልጣኑ ከተሰጡት ኃላፊነቶች አንዱ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመቀናጀት የሥርዓተ ምህዳር አገልግሎት ክፍያ የአሰራር ሥርዓት መዘርጋት እና አተገባበሩን መከታተልና መቆጣጠር መሆኑን ገልፀዋል።
በሥርዓተ ምህዳር አገልግሎት ክፍያ አዋጅ አዋጅ ቁጥር 1401/2018ዓ.ም መሰረት የሥርዓተ ምህዳር ተጠቃሚዎች ለሥርዓተ ምህዳር አገልግሎቶች አቅራቢዎች ክፍያ የሚፈፀምበት አሰራር ነው።
አቶ ንጉሱ በገለፃቸው አዋጁን ወደ መሬት ለማውረድ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ቅንጅት እንደሚፈልግ ገልፀው ተከታታይነት ያለው የአቅም ግንባታ ስራዎች ማከናወን እና ተቋማዊ አደረጃጀቶችን በፍጥነት ሟሟላት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ላይ የሥርዓተ ምህዳር አገልግሎት ክፍያ አዋጅ ቁጥር 1401/2018 ይዘትና አተገባበር፣በመዳወላቡ ዪንቨርስቲ የተካሄዱ የምርምር ውጤቶች እንዲሁም በሥርዓተ ምህዳር አገልግሎት ክፍያ የኬንያ ተሞክሮ ቀርቧል።
በመድረኩ ላይ በአዋጁ አፈፃፀም ላይ የፓናል ውይይት የተካሄደ ሲሆን ከየህዝብ ተወካዮች ቋሚ ኮሚቴዎች፣ከዪንቨርሲቲ ምሁራን እንዲሁም መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ተሳትፈውበታል።