ኡደታዊ ስነምጣኔ(ETHIOPIA CIRCULAR ECONOMY HOTSPOT 2025) አውደ ጥናት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
መስከረም 21/2018 ዓ.ም
*@***
በኢትዮጵያ አዘጋጅነት ኡደታዊ ስነምጣኔ(ETHIOPIA CIRCULAR ECONOMY HOTSPOT) አውደ ጥናት እየተካሄደ ነው ።
ኡደታዊ ስነምጣኔ ማለትም ቆሻሻ መቀነስ፣ ቆሻሻን መልሶ የመጠቀም እና የአወጋገድ ሥርዓት ዘላቂና አካታች ኢኮኖሚ ለመገንባት ወሳኝ ሚና አለው ሲሉ ኢንጂነር ለሊሴ ነሜ ገለጹ።
የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ለሊሴ ነሜ በወቅቱ እንደገለጹት፤ ኡደታዊ ስነምጣኔ ዘላቂና የተፈጥሮ ሀብትን በአግባቡ የመጠቀምና ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ ወሳኝ ሚና እንዳለው ገልጸዋል ።
ኢትዮጵያ የዓመቱን የአፍሪካ ኡደታዊ ስነምጣኔ ሆትስፖት ለማዘጋጀት ተመርጣለች ያሉ ሲሆን፤ ኡደታዊ ኢኮኖሚ ቆሻሻን መልሶ መጠቀም ካልተቻለም በአግባቡ መወገድ የሚቻልበትን ሥርዓት መዘርጋት መሆኑን አስረድተዋል።
በኢትዮጵያ ስርዓት በመዘርጋት ቆሻሻን በአግባቡ ጥቅም ላይ መዋልና ለማስተዳደር ሀገራዊ ኡደታዊ ስነምጣኔ ስትራቴጂ እና የደረቅ ቆሻሻ አዋጅ መውጣቱን ተናግረዋል ።
ኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ስራን ከፍተኛ ትኩረት አድርጋ እየሰራች መሆኑን ገልጸው፤ የኮርደር ልማት፣ ጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ፣ የአረንጓዴ አሻራና የወንዝ ዳርቻ ልማት ተጠቃሽ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ዘርፉ ለእድገት ሽግግር፣ ለስራ እድል ፈጠራ፣ ለኢኮኖሚያዊ አቅም ግንባታ፣ ሴቶችን ለማብቃት እንዲሁም አዳዲስ የኢኮኖሚ እሳቤ ለማጠናከር እንደሚያግዝ ተናግረዋል።
የህዝብ ግንዛቤን ለማሳደግ እስከ አሁን ሀገሪቱ 30 ሚሊየን ኢትዮጵያዊያን ተደራሽ ያደረገ ጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ አድርጋለች ያሉት ዋና ዳይሬክተሯ፤ አካባቢን መጠበቅና ጽዳትን ማረጋገጥ ባህል ማድረግ እንደሚገባም ጠቁመዋል።
ቆሻሻን በአግባቡ መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋል እና ለማስወገድ የአምራች እንዱስትሪ ፣ የከተሞች አስተዳደር እና የግለሰብ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል ።
የከተሞች ልማት ውጤታማ የሃብት አጠቃቀም ዘላቂ አካባቢ አያያዝና አረንጓዴ ልማት ዙሪያ የምታደርገውን ተሳትፎ መልካም አጋጣሚ የሚፈጥር ነው፡፡
በኢትዮጵያ ፊንላንድ አምባሳደር ሚስ ስንካ አንትላ የፊንላንድን ተሞክሮ የቀረቡ ሲሆን በዘርፉ የሀገራቸው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥ ገልጸዋል ።
በአውደ ጥናቱ ላይ በኡደታዊ ስነምጣኔ( CIRCULAR ECONOMY) የተሻለ ፈጠራ ያላቸው ግለሰቦች እና ድርጅቶች የሽልማት እና እውቅና ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል ።
በመድረኩ ከሀገር ውስጥና ከአፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ ፖሊሲ አውጪዎች፤ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ባለድርሻ አካላት፤ የኢንደስትሪ ተቋማት፤ የፈጠራ ባለሙያዎች እንዲሁም የፌደራል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
===============================
የኢፌዲሪ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን
ቀጣዮችን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ