በክብርት ኢ/ር ለሊሴ ነሜ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የተመራ ልዑካን ቡድን ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል " የፅዱ ኢትዮጵያ ባህል ማድረግ “ክልላዊ ንቅናቄ ማስጀመሪያ መድረክን ለመሳተፍ ሆሳዓና ከተማ ሲደርስ በክልሉ የአከባቢ ጥበቃ ቢሮ ሃላፊ አቶ አብርሃም ሜጫ እንዲሁም በፖሊስ ኦኬስትራ ባንድ አቀባበል ተደረገለት። ነገ ሰኔ 18/2017 ዓም በሚጀመረው ንቅናቄ መድረክ ከፍተኛ የክልሉ አመራሮች እና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ይጀመራል።



