ሲዳማ ክልል "ፅዱ ኢትዮጵያን ባህል ማድረግ" ክልላዊ ንቅናቄ ሀዋሳ ከተማ ክቡር ፕሬዘዳንት አቶ ደስታ ሊዳሞ እና ክብርት ኢ/ር ለሊሴ ነሜ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር በተገኙበት በይፋ በፅዳት፣ ችግኝ ተከላና የፓናል ውይይት ተጀምሯል። በመድረኩ
የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የዞን አመራሮች የሀገርና የሀይማኖት አባቶች፣ የተማሪ ተወካዪች፣ የሚዲያ ተቋማት አመራሮች ጥሪ የተደረገላቸው የህብረተሰብ ተወካዮች ተገኝተዋል።
በመክፈቻ መድረኩ ላይ ክቡር ፕሬዘደንቱ ሁሉም ዞኖችና የከተማ መስተዳድሮች የተሰጠውን ተልዕኮ በቁልፍ የክረምት ወቅት ስራዎች ጋር በማቀናጀት ለትግበራው አመራር፣ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባው አመራር ሰጥተዋል:: በክልሉ በአካባቢ ጥበቃ ዘርፍ ውጤታማ ለመሆን እየሰሩ ላሉ ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞችና ባለሀብቶች እውቅና ተሰጥቷል።
በመድረኩ ላይ የክልሉ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተሩ ክብር አቶ ሽታዪ ኡመያ የንቅናቄው ዕቅድ ሰነድ ሲያቀርብ በስድስት ወራት ንቅናቄ ውስጥ በክልሉ አንድ ነጥብ ሁለት ሚሊዮን የህብረተሰብ ክፍልን ገፅ ለገፅ እንዲሁም አራት ነጥብ አምስት ሚሊዮን በተለያዩ መደበኛና ማህበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም የህብረተሰብ ክፍሎችን ተደራሽ ለመሆን ዕቅድ ግብ መጣሉን ገልፀዋል። ዋና ዳይሬክተሩ ከግንዛቤ ማስጨበጫ በተጨማሪም የአካባቢ ህግ ተከባሪነትን ለማረጋገጥ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰሩ አብራርተዋል።







====================================
የኢፌዲሪ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን
ቀጣዮችን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ
============================================