ሦስተኛው ዙር ክልል አቀፍ የአካባቢ ብክለት መከላከል ንቅናቄ ''ፅዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ'' በሚል መሪ ቃል በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ በይፋ ተጀመረ ::
ሐምሌ 30/2018 ዓ.ም
አሶሳ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
''ፅዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ''ሶስተኛው ዙር ክልል አቀፍ የአካባቢ ብክለት መከላከል ንቅናቄ በቤንሻንጉል ጉሙዝ አሶሳ ከተማ የክልሉ ም/ቤት ዋና አፈጉባኤ ክብርት ወ/ሮ አስካለች አልቦሮ፣ ክብርት ወ/ሮ ፍሬነሽ መኩሪያ የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር ፣የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የአሶሳ ከተማ ከንቲባ ፣ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የተለያዩ የግሉ ዘርፍ ማህበራት፣ የፀጥታ አባላት፣ የዞንና የወረዳ አመራሮች የት/ቤቶች ተማሪዎችና መምህራን፣ የአካባቢ ተዋቂ የሀገር ሽማግሌዎችና የባህል አባቶች፣ የሃይማኖት አባቶች እና የአሶሳ ከተማ ነዋሪዎች በተገኙበት በተለያዩ ኩነቶች በይፋ ተጀመረ።
የክልሉ ም/ቤት ዋና አፈጉባኤ ክብርት ወ/ሮ አስካለች አልቦሮ የክልል አቀፍ የንቅናቄ መድረኩ በንግግር በይፋ ባስጀመሩበት ወቅት
ማንኛውም የሚሰሩ የልማት ሥራዎች አካባቢ ደህነቱንና የተፈጥሮ ሀብት ሥርዓተ ምህዳሩን በጠበቀ መንገድ እንዲከናውኑ መልዕክት አስተላለፉ።
በከተሞችም ሆነ በገጠር የሚሰሩ የልማት ሥራዎች በሰዎች ጤና፣ በአካባቢ ደህንነት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንይፈጥሩ እንዲሁም የአካባቢ ሥርዓተ ምህዳሩን እንዳያዘቡ በመንግስት የወጡ ህጉችንና አሰራሮችን መሠረት በማድረግ እንዲፈፀም፤ እንደ ሀገር የተጀመረው የፅዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ ንቅናቄ በክልላችን ውጤታማ እንዲሆን በአግባቡ እየተመራ በቅንጅት መሠራት እንዳለበት በአጽዕኖት አሳስበዋሉ።
የነገ ትውልድን ለመታደግ ዛሬ አካባቢ መጠበቅ ወሰኝ በመሆኑ ሁሉም የልማት ተቋማት፣ አምራቾች፣ በመዕድን ቁፋሮ ሥራ ላይ የተሰማሩ ተቋማት ፣የከተማ አስተዳዳሮችና በየደረጃው የሚገኙ መዋቅሮቻችን ንቅናቄውን በባለቤትነት መምረት ሂደቱንም በየወቅቱ እየገመገሙ መሄድ እንዳለባቸው፤ ግንዛቤ ተፈጥሮም የአካባቢን ህግን በማያከብሩ አካላት ላይ ተጠያቂነትን ማስፋን እንደሚገባም ግልጽ አመራርና የአፈፃፀም አቅጣጫ ሰጥተዋሉ።
የፌደራል አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ክቡርት ወ/ሮ ፍሬነሽ መኩሪያ ባስተላለፉት መልዕክት አካባቢን ከብክለት መከላከል ማህበራዊና ኢኮኖሚ ልማትን ቀጣይነት ማረጋገጥ በመሆኑ ከዚህ በፍት እንደ ሀገር በተካሄዱ ሁለት ዙር ንቅናቄዎች በአካባቢ ጥበቃ፣ በተፈጥሮ ሀብቶች አጠባበቅ መሻሻል የተገኙ ውጤቶችን በጋራ በመገምገም ውስንነቶችን ደግም በመለየት በቀጣይ ለማስተካከል እንዲቻል ፤ እስካሁን በንቅናቄዎቹ በተፈጠረው ግንዛቤ በየአካባቢው የተፈጠረውን ከፍተኛ መነቃቃትን በመጠቀም በቀጣይ ለበለጠ ውጤት በትጋትና በቅኝጅት መስራት እንደሚገባውም አሳስበዋሉ።
ዛሬ በሚካሄደው ክልል አቀፍ የአካባቢ ብክለት መከላካል ንቅናቄ መድረክም በቀጣይ ሶስት ወራት በፕላስቲክ ፣ በአደገኛ ኬምካሎችና ቆሻሻ እና በድምጽ ብክለትን ለመከለከል በቅንጅት ነሚሰራ በመሆኑ ሁሉም የሚመለከታቸውን አካላትን በማቀናጀት መፈፀም እንደሚጠበቅ አሳስበዋሉ።
ክቡር አቶ ሉቁማን አብድርቃድርን የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር በበኩላቸው በስተላለፉት መልዕክት አካባቢ መጠበቅና ለቀጣይ ትውልድ ንጽህና ምቹ አካባቢን መፍጠር የሁሉም ባለድርሻ አካላትና የዜጎችም ሁሉ ኃላፊነት በመሆኑ በዚህ ፅዱ ኢትዮጸጵያ ለትውልድ ንቅናቄ በመሳተፍ የበኩላቸው እንዲወጡ ጥሪ አስተላልፈዋሉ።
በክልሉ የአካባቢ ብክለት ለመከለከል የሚያስችሉ ሰፍ ግንዛቤ ከመፍጠራችን በላይ የህግ ማስከበር ሥራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኙ ገልፀው ዛሬ በይፋ የሚጀመራው የአካባቢ ብክለት መከላከል ንቅናቄ ውጤታማ እንዲሆን ሁሉም የክልሉ ባለድርሻ አካላት የተለመደው ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋሉ።
በመጨረሻም መድረኩም የፌደራልና ክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እና የተለያዩ የህብረሰብ ክፍሎች እና የአሶሳ ከተማ ነዋሪዎች በተገኙበት በከተማ ፅዳት ዘመቻ ፣ በአካባቢ ብክለት ዙሪያ የመወያያ ሰነድ ቀርቦ ውይይት በማድረግ እና በዕለቱ ክቡር እንግዳ የሥራ አመራርና አቅጣጫ ተሰጥቶ መድረኩ ተጠናቋል ።