ሀገራዊ ሰርኩለር ኢኮኖሚ ፍኖተ ካርታ የኢትዮጵያን ዘላቂ ልማት ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና እንዳለው ተገለጸ።
መጋቢት 16/2017 ዓ.ም
++++++++++++++++++++++
የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለ።ሥልጣን እየተዘጋጀ ያለውን ሀገራዊ ሰርኩለር ኢኮኖሚ ፍኖተ ካርታ ከባለድርሻ አካለት ጋር እስከአሁን የዝግጅት ሂደት አፈጻጻም ተገመገመ።
ሀገራዊ ሰርኩለር ኢኮኖሚ ፍኖተ ካርታ የተፈጥሮ ሀብትን በአግባቡ መጠበቅና ቆሸሸን መልሰው መጠቀም መስመር በመሆኑ የሀገራችንን ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና እንዳለው በግምገማ መድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክብርት እንጂነር ሌሊሴ ነሜ ሀገራዊ ሰርኩለር ኢኮኖሚ ከሀገራዊ የልማት ዕቅድ ጋር ሙሉ በሙሉ የተጣጣመ ፣ የሴክተሮች ቅንጅት ያካተተ እና ሰው ተኮር ሆኖ እየተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል ።
በከተሞች ማስፋፋት ፣ በህዝብ ቁጥር እድገት እና የአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭነት ጋር ተያይዘው ልከሰቱ የሚችሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ሀገራዊ ሰርኩለር ኢኮኖሚ ሚና ከፍተኛ መሆኑን እክብርት ኢንጂነር ሌሊሴ ነሜ አብራርተዋል ።
ዋና ዳይሬክተሯ አክለውም ሰርኩለር ኢኮኖሚ ፍኖተ ካርታ የተፈጥሮ ሀብቶቻችን በዘላቂነት መጠበቅ እና መጠቀም ፣ የስራ እድል ለመፍጠር ፣ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በአጠቃላይ የኢትዮጵያን ዘላቂ ልማት ለማረጋገጥ የሚረዳ መሆኑን አብራርተዋል ። በሀገራችን እተገበሩ ያሉ ስማርት ከተሞች ፣ የኮርደር ልማት፣ አረንጓዴ አሻራ እና ጽዱ ኢትዮጵያ የልማት ስራዎች ከሰርኩለር ኢኮኖሚ ፍኖተ ካርታ ጋር የሚጣጣሙ መሆናቸውን ዋና ዳይሬክተሯ አስረድተዋል ።
በግምገማ መድረኩ ላይ የተገኙት በኢትዮጵያ የፊንላንድ አምባሳደር ሚስ ሲኒካ አንቲላ ሰርኩላር ኢኮኖሚ አቅጣጫ መከተል ቆሻሻን በአግባቡ መያዝ ብቻ ሳይሆን ስራ እድል ለመፍጠር፣ ለኢኮኖሚን እድገት ፣ሙቀት አማቂ ጋዞችን ለመቀነስ እንደሚያስችል በመግለጽ ሀገራቸው በዘርፉ ያላትን ተሞክሮ ለማካፈል እና አቅም ለመገንባት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ የአፍሪካ ልማት ባንክ ተወካይ ሚስተር ጆን ቦስኮ ቡከና ኢትዮጵያ ለአካባቢ ጥበቃ እና ለዘላቂ ልማት ያለትን ቁርጠኝነት ከፍተኛ መሆኑን በመግለጽ የአፍረካ ልማት ባንክ ድጋፉን አጠናክረው እንደሚቀጥል ገልጸዋል ።
በአውደ ጥናቱ ላይ በባለሞያዎች ረቂቅ ፍኖተ ካርታ ቀርበው ውይይት በመካሄድ ግብአት ተገኝቷል ።
=========================================
የኢፌዲሪ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን
ቀጣዮችን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ